Jump to content

አሉምኒ ፖርታል ዶችላንድ

ከውክፔዲያ

አሉምኒ ፖርታል ዶችላንድ ከትርፍ ነፃ የሆነና በጀርመን አገር ስልጠና ላደረጉ ሰዎች የተዘጋጀ ማህበራዊ ድረ ገፅ ነው። ማንኛውም በጀርመን አገር ጥናት፤ ሪሰርች ያደረገ፤ ስራ የስራ ወይም በጀርመን አገርም ሆነ በውጭ አገር ማንኛውንም አይነት የቋንቋም ሆነ ሌላ አይነት ስልጠና ያደረገ አሉምኑስ ሊጠቀምበት የሚችል ድረ ገፅ ነው። ፖርታሉ ለግልም ሆነ ሙያን ላስመለከተ ጉዳይ የተዘጋጀ ነው። ስኮላርሺፕ ላገኙም ሆነ ላላገኙ፤ በአለም አቀፍ የጥናት ፕሮግራሞች ለተሳተፉም ሆነ ላላልተሳተፉ ግለሰቦች ክፍት የሆነ መድረክ ነው። የግል ድርጅቶች በነፃ ድረ ገፁን ለመጠቀም ይችላሉ። ፕሮጀክቱ በአምስት የጀርመን አገር ድርጅቶች እንዲሁም በጀርመን አገር መንግስት ትብብር ተዘጋጅቷል።

የአሉምኒ ፖርታል ዶችላንድ ድረ ገፅ በእንግሊዝኛ እና በጀርመንኛ ቋንቋ ተዘጋጅቷል። ኰሚውኒቲው ውስጥ በተለያዩ ቋንቋዎች መልእክት መለዋወጥ ይቻላል።

አሉምኒ ፖርታል ዶችላንድ ለጀርመን አሉምኒዎች ከሎሎች አሉምኒዎች እንዲሁም ከጀርመን አገር ጋር ግንኙነት ካላቸው ድርጅቶች ጋር ግንኙነት እንዲኖራቸው ይረዳቸዋል።

ከተለያዩ የኰሚውኒቲ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ፖርታሉ አለም አቀፍ የሆኑ የስራ እንዲሁም የሙያ ማታወቂያዎችን ባህልትምህርትሳይንስኢኮኖሚን ያስመለከተ የስነ ፅሁፍ ክፍል አለም አቀፍ የሆኑ ዝግጅቶችን ያስመለከተ ክፍል በተጨማሪም ጀርመንኛ ቋንቋን መማሪያ መሳሪያዎች ያስመለከቱ ፕሮራግሞችን አካቷል።

አሉምኒ ፖርታል ለድርጅቶች በጀርመን አገር የሰለጠኑ አለም አቀፍ የሆኑ ኤክስፐቶችን ማግኛ መንገድ ሊሆናቸው ይችላል። ድረ ገፁ እነዚህ ድርጅቶች ኤክስፐርቶችን እንዲሁም ቢዝነስ ፓርትነሮችን የሚያገኙበት መድረክ ነው።

አሉሚኒዎች ለረዥም ጊዜ ከአገር ውጭ በመሄድ የስራ ልምዳቸውን ለማዳበር ሙከራ ሲያደጉ ቆይተዋል። ይህም ቢሆን ወደ 80% የሚደርሱ ወደ ጀርመን አገር ለጥናት ከሚሄዱት መካከል ወደ 14,000 የሚጠጉት የራሳቸውን ወጪ ችለው የሚንቀሳቀሱ ናቸው። ከነዚህ ግሩፖች ጋር ግንኙት ለመፍጠር አስቸጋሪ ሙከራ ነበር።

አሉምኒ ፖርታል ዶችላንድ ከማንኛውም ድርጅት ለሚመጡ ለጀርመን አገር አሉምኒዎች የተዘጋጀ ድረ ገፅ ነው። ዋነኛው አላማ እነዚህን ግለሰቦች ነፃ ትምህርት ሰጪ ድርጅቶችን እንዲሁም በጀርመን አገር የሰለጠኑ ተቀጣሪዎችን የሚፈልጉ ድርጅቶን አንድ ላይ ማምጣት ነው።

የፕሮጀክቱ ፅንሰ ሃሳብ ከተጀመረበት 2008 እ.ኤ.አ. ጀምሮ 65.977 አባላት 1.369 ድርጅቶች 306 ዩኒቨርቲዎች 392 ክፍት የራ ቦታ ማስታወቂያዎች 3.876 የግል ፐሮፋይሎች 915 ግሩፖችን 1.541 ብሎጎችን አጠቃሎ ይዟል (April 2013 እ.ኤ.አ.)

የድረ ገፁ ውስጣዊ ይዘት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አሉምኒ ፖርታል ዶችላንድ ሁለት ክፍሎች አሉት፤ ኦንላይን ኮሚኒቲ እና ኢንፎ ፖይንት።

ኦንላይን ኮሚኒቲ የማህበራዊ መገናኛ ክፍል ነው። ይህ ክፍል ፖርታሉ ውስጥ ለተመዘገቡ አባሎች ብቻ ክፍት ሲሆን እነዚህ አባሎች ከሌሎች አባሎች እንዲሁም ከድርጅቶች ጋር በግሩፖች በብሎጎች በፕሮፋይሎች በተጨማሪም በፎረሞች ወዘተ በመጠቀም ሃሳባቸውን ለመለዋወጥ የሚችሉበትን መንገድ ፈጥሮላቸዋል።

ኢንፎ ፖይንት ላልመዘገቡ አባላትም ክፍት የሆነ መድረክ ነው። ይህ መድረክ ውስጥ ከጀርመን አገር ጋር ግንኙነት ያላቸውን መልእቶች ማግኘት ይቻላል። ተጠቃሚዎች የጀርመንኛ ቋንቋ ችሎታቸውን የጎተ ኢንስቲቲዩት በሚሰጣቸው ፕሮግራሞች በመጠቀም ለማሻሻል ይችላሉ። በኢንፎ ፖይንት ውስጥ ሙያቸውን ወይም ትምህርታቸውን ለመቀጠል የሚፈልጉ ግለሰቦች እንዲሁም አለም አቀፍ ስራ የሚፈልጉ የተለያየ ኢንፎሜሽን ለማግኘት ይችላሉ። የኤዲቶሪያል ክፍሉ ውስጥ ስለ ኢኮኖሚ ሳይንስ ጥናት ባህል እና ወዘተ ማንበብ ይቻላል።

የጀርመን ድርጅቶች በኢንፎ ፖይንት በመጠቀም በጀርመን አገር ውስጥ የሰለጠኑ አዲስ ተቀጣሪዎችን ለማግኘት ይችላሉ። ድርጅቹ አሉምኒ ፖርታል ውስጥ ከተመዘገቡ በኋላ ክፍት የስራ ቦታቸውን ማስተዋወቅ ሬዙሜዎችን ማመሳሰል እንዲሁም ድርጅታቸውን ያስመለከቱ አዲስ ዜናዎችን በነፃ ማስተዋወቅ ይችላሉ።

አጋሪ ድርጅቶች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አምስቱ ዋነኛ ከትርፍ ነፃ የሆኑ አሉምኒ ፖርታል ዶችላንድን በመፍጠር በመደገፍ እንዲሁም በማስተዋወቅ እየረዱ ያሉ ድርጅቶች የሚቀጥሉት ናቸው፤

  • አሌክሳንደር ፎን ሁምቦልት ፋውንዴሽን (AvH; in German: Alexander von Humboldt-Stiftung)
  • የጀርመን የእድገት ትብብር ድርጅት [GIZ; Deutsche Gesellschaft für Internationale Zusammenarbeit]]
  • የጀርመን የትምህርት እና የሙያ ልውውጥ ፕሮግራም (DAAD; Deutscher Akademischer Austauschdienst)
  • ጎተ ኢንስቲቲዩት [GI; Goethe-Institut]

በቁጥር ከአስር የበለጡ ስራቴጂክ አባሮች ከላይ የተጠቀሱትን የአሉምኒ ፖርታል ዶችላንድን ስፖንሰሮች በመደገፍ ላይ ይገኛሉ። ከነዚህም መካከል የጀርመን አገር ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፤ የጀርመን አገር ትምህርት ሚኒስትር እንዲሁም የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች እንደ ፍሪድሪሽ ኤበርት ኮንራድ አደናወር እና ሃይንሪሽ ቦል ድርጅቶች ይገኙበታል።

ሌሎች ሊንኮች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]