Jump to content

አማ አታ አዪዶ

ከውክፔዲያ

ክሪስቲና አማ አታ አዪዶ በማርች 23፣ 1942 እ.ኤ.አ. ጋና ውስጥ ተወለደች። ትምህርቷን በዌስሊ የልጃገረዶች ትምህርት ቤት፣ በመቀጠልም በጋና ዩኒቨርስቲ ተከታትላ በ1964 ዓ.ም በእንግሊዝኛ ቋንቋ የመጀመሪያ ዲግሪዋን ተቀብላለች። የመጀመሪያ የድርሰት ስራዋ የሆነውን «The Dilemma of a Ghost»ን በዚያ ዓመት ለማጠናቀቅ የበቃች ሲሆን ይሄው ድርሰቷ በሎንግማን አሳታሚ ድርጅት አማካይነት በቀጣዩ ዓመት ታትሞላታል።

አዪዶ በልብ-ወለድ ደራሲነት ብቻ አይደለም እውቅናን ያተረፈችው፤ በጸሃፌ-ተውኔትነት እና ገጣሚነትም እንጂ። ጽሁፎቿ በአብዛኛው የዘመኑ የአፍሪካ ሴቶች ስላላቸው ሚና እና የምእራባዊው ባህል ስለሚያሳድርባቸው ኢርቱእ ተጽኖ ላይ የሚያተኩሩ ናቸው።

አዪዶ በ1982 የጋና የትምህርት ሚኒስትር ሆና ብትሾምም በስራው ላይ የቆየችው ለ18 ወራት ያህል ብቻ ነው። በአሁኑ ወቅት በብራውን ዩኒቨርስቲ የአፍሪካ ጥናት ክፍል ውስጥ ተጋባዥ ፕሮፌሰር በመሆን ትሰራለች።

የሥነ-ጽሁፍ ሥራዎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
  • Dilemma of a Ghost (1965)
  • Anowa (በጋና አፈታሪክ ላይ ተመስርቶ የተጻፈ ተውኔት፣ 1970)
  • No Sweetness Here (የአጫጭር ታሪኮች መድብል፣ 1970)
  • Our Sister Killjoy (1977)
  • Someone Talking to Sometime (የግጥም መድብል፣ 1986)
  • The Eagle and the Chicken (1986)
  • Birds and Other Poems (የህጻናት መጽሃፍ፣ 1988)
  • Changes: A Love Story (1991)
  • An Angry Letter in January (የግጥም መድብል፣ 1992)
  • The Girl Who Can and Other Stories (1997)