አረንጓዴ ዋቅላሚዎች
አረንጓዴ ዋቅላሚዎች ሰፊ የሆነ ኢመደበኛ የዋቅላሚዎች መደብ ነው። በውስጡ አሁን በተለያዩ መደቦች ውስጥ የሚገኙትን ክሎሮፋይታንና ካሮፋይታን የሚያቅፍ ነው።
አረንጓዴ ዋቅላሚዎች በአብዛኛው ሁለት ልምጭት ያላቸው አንድህዋሴ እና ኩይዋሳዊ ባለልምጭት ዝርያዎችን፣ የተለያዩ ኩይዋሳዊ፣ ድቡልቡል እና ዘሃዊ ቅርፅ ያላቸው ዝርያዎችን እንዲሁም ትላልቅ ባለብዙ ህዋስ የባህር አረሞችን ያካትታሉ፡፡ ብዛታቸው ወደ 22,000 ገደማ የሚሆኑ የአረንጓዴ ዋቅላሚ ዝርያዎች አሉ፡፡[1]
አንዳንድ የአረንጓዴ ዋቅላሚ ዓይነቶች፣ በተለይም ከትሬቦክሲያ እና ትሬንቴፖህሊያ ቡድኖች፣ ከፈንገስ ጋር አብረው በመኖር የድንጋይ ሽበት ይፈጥራሉ። አብዛኛውን ጊዜ በድንጋይ ሽበት ውስጥ ያሉ ፈንገሶች በራሳቸው ሊኖሩ አይችሉም፣ ነገር ግን ዋቅላሚዎቹ ብዙውን ጊዜ በተፈጥሮ ለብቻቸው ሊኖሩ ይችላሉ። ትሬንቴፖህሊያ በእርጥብ አፈር ላይ፣ በድንጋይ ላይ ወይም በዛፍ ቅርፊት ላይ በራሱ የሚያድግ የአረንጓዴ ዋቅላሚ አይነት ነው፣ ወይም በ ግራፊዳሲዬ ቤተሰብ ውስጥ የድንጋይ ሽበት አካል ሊሆን ይችላል። ሌላው የአረንጓዴ ዋቅላሚ አይነት ፕራሲዮላ ካሎፊላ በመሬት ላይ ይኖራል።[2] ፕራሲዮላ ክሪስፓ ደግሞ በባሕር ዳርቻዎች የሚበቅል ሲሆን እና እንደ አንታርክቲካ ባሉ ቦታዎች በተለይም በወፎች መኖሪያ ስፍራ አቅራቢያ ትላልቅ ምንጣፎችን መፍጠር ይችላል።[3]
አረንጓዴ ዋቅላሚዎች በታይላኮይድ ድርድር ውስጥ ደማቅ አረንጓዴ ቀለም የሚሰጧቸውን ኤ እና ቢ የተሰኙ አረንጓዴ ሐመልሚሎችን እንዲሁም ተጨማሪ ቀለማት ቤታ ካሮቲን (ደማቅ ብርትኳናማ)እና ዛንቶፊሎች (ቢጫ) ቀለም ያቀፈ አረንጓቀፍ አላቸው።
- ^ Guiry MD (October 2012). "How many species of algae are there?". Journal of Phycology. 48 (5): 1057–63.
- ^ Holzinger, A.; Herburger, K.; Blaas, K.; Lewis, L. A.; Karsten, U. (2017). "The terrestrial green macroalga Prasiola calophylla (Trebouxiophyceae, Chlorophyta): Ecophysiological performance under water-limiting conditions". Protoplasma. 254 (4): 1755–1767. doi:10.1007/s00709-016-1068-6. PMC 5474099. PMID 28066876
- ^ Carvalho, Evelise L.; MacIel, Lucas F.; MacEdo, Pablo E.; Dezordi, Filipe Z.; Abreu, Maria E. T.; Victória, Filipe de Carvalho; Pereira, Antônio B.; Boldo, Juliano T.; Wallau, Gabriel da Luz; Pinto, Paulo M. (2018). "De novo Assembly and Annotation of the Antarctic Alga Prasiola crispa Transcriptome". Frontiers in Molecular Biosciences. 4: 89. doi:10.3389/fmolb.2017.00089. PMC 5766667. PMID 29359133