Jump to content

አሪንጎ

ከውክፔዲያ
አሪንጎ
የአሪንጎ ታላቅ በር፣ በ1850ወቹ በመፈራረስ ላይ አያለ
አሪንጎ is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
አሪንጎ

11°52′ ሰሜን ኬክሮስ እና 37°58′ ምሥራቅ ኬንትሮስ


አሪንጎደብረ ታቦር 10 ኪ.ሜ ሰሜን ምዕራብ፣ እንዲሁ ከጣና ሐይቅ 45 ኪሎ ሜትር በስተምስራቅ የምትገኝ ጥንታዊ ከተማ ናት፡፡ አሪንጎ በታሪክ ጎላ ብላ መታየት የጀመረችው አጼ ፋሲለደስ ዘመን የነበር ሲሆን፣ በዚችው ከተማ የሃይማኖት ጉባኤዎችን በመጥራትና በየክረምቱ እየሄደ ጊዜውን ያሳልፍ እንደነበር ይጠቀሳል። ታላቁ እያሱ አሪንጎን ይወድ እንደነበርና ለዚህ ምክንያቱ የአካባቢው ቀሳውስት ከነበራቸው የታሪክሙዚቃ እና ቅኔ የጠለቀ እውቀት አንጻር እንደነበር ዜና መዋዕላቸው ይዘግባል። ስለሆነም በ1683ዓ.ም. ቤተመንግስት ተገንብቶ ነገስታቱ በየክረምቱ እየመጡ ማርፊያቸው ሆነች። ኢትዮጵያን በዚያው ዘመን ጎብኝቷት የነበረው ፈረንሳዊው ሃኪም ጃኩስ ፖንቼት አሪንጎ ከጎንደር ከተማ የማትተናነስ እንደነበርች ዘግቧል[1]። በወቅቱ ከ4000 እስከ 5000 የንጉሱ ሰራዊት በቋሚ ይሰፍሩባት ነበር። ከታላቁ እያሱ እስከ በካፋ ዘመን ድረስ ነገስታቱ ክረምታቸውን በዚህች ከተማ እያሳለፉ ከተማዋም እያደገች ትሂድ እንጂ ከበካፋ በኋላ ቀስ በቀስ እየተረሳች ሄዳ ለመፈራረስ በቃች። በአሁኑ ወቅት በአካባቢው ብዙ የፈራረሱ ቤቶች፣ የአሳማ ማርቢያወች፣ የውሃ ማጠራቀሚያወች፣ ከዚያ ዘመን የሚመንጩ ይገኙባታል[2]። ነገር ግን የአካባቢው ህዝብ የፍራሹን ድንጋይ ለቤት መስሪያነት ስለሚገለገልበት አብዛኞቹ ፍራሾች ምን አይነት እንደነበሩ እስኪያዳግት ድረስ ጠፍተዋል። አፍ መቁረቢያ የሚባለው ግምብ ብቻ ከሁሉ በተሻለ መልኩ ተይዞ ይገኛል[3]



የአሪንጎ ውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳ- በአሁኑ ዘመን
  1. ^ Punkhurst,Richard Encyclopaedia Aethiopica (Harrasowitz Verlag) 2003
  2. ^ Hespeler-Boultbee, A Story in Stones: Portugal's Influence on on culture and architecture in the Highlands of Ethiopia 1493-1634, CCB Publishing,2011, page 116,
  3. ^ Munro-Hay,Stuart C. Ethiopia, the unknown land: a cultural and historical guide, page 77