አሰፋ አባተ
Appearance
አሰፋ አባተ ደግሞውም «የማሲንቆው አባት»ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ድምፃዊ ነበር።
አሰፋ አባተ በ፲፱፻፳፱ ዓ.ም. በወሎ ክፍለ ሀገር የጁ ሳንቃ ቀበሌ ተወለደ። አሰፋ ፱ ዓመት እንደሞላው በድምፁ ግሩምነት ተደንቆ በደሴ ቤተ መንግሥት ሥራ ጀመረ። ከዚያም በ፲፱፻፵፩ ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በሀገር ፍቅር ማህበር ተቀጠረ።
አሰፋ አባተ በሙዚቃው ዓለም ለአጭር ጊዜ እስከቆየበት ጊዜ ድረስ ፶ የሚሆኑ ዜማዎችን ተጫውቷል። ከነዚህ መካከል «ዓሳ አበላሻለሁ ዓባይ ዳር ነው ቤቴ» እና «የማትበላ ወፍ በጭራ ተይዛ» ይጠቀሳሉ።
- ናሽናል ቢብሊዮግራፊ ቡድን፣ የአንጋፋ አርቲስቶች መዝገበ የሕይወት ታሪክ፣ መጋቢት ፳፻፣ ገጽ 18 Archived ሴፕቴምበር 29, 2011 at the Wayback Machine