አበሻ ስም

ከውክፔዲያ

የአበሻ ስምኢትዮጵያ[1] እና ኤርትራ[2] የሚሰጥ ሲሆን አወቃቀሩ ከአረብ እና አይስላንድ አወቃቀር ጋር ተመሳሳይ ነው። አንድ ልጅ ሲወለድ ከሚወጣለት ስም በተጨማሪ በአባቱ እና በአባቱ ወንድ አያት ስም ይጠራል። በተለምዶ አሰያየሙ በአባት በኩል ቢሆንም በኤርትራ ውስጥ በእናት በኩል መሆን እንደሚችል የሚፈቅድ ሕግ ጸድቋል።

የአበሻ ስም እንደ ምዕራባውያን የመጨረሻ ወይም የቤተሰብ ስም (እንግሊዝኛ፦ last name / family name) የለውም። በተጨማሪም ሴቶች ሲያገቡ ስማቸውን አይቀይሩም። በውጭ አገር የሚገኙ ዳያስፖራ አንዳንዴ የአባት ስማቸውን የመሃል ስም (እንግሊዝኛ፦ middle name) እና የአያት ስምን ደግሞ የቤተሰብ ስም አድርገው ይጠቀማሉ።

ማመዛገቢያ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ Spencer, John H (2006). Ethiopia at bay : a personal account of the Haile Selassie years. Hollywood, CA: Tsehai. pp. 26. ISBN 1-59907-000-6. http://books.google.com/books?id=w5q7NV-vSPwC&pg=PA26&lpg=PA26&dq=Ethiopian+Patronymics&source=bl&ots=pWq8coDGER&sig=vqOSosI0FEjxhRq-nInSxZ2Y7kc&hl=en&sa=X&ei=lcjsUKGwD-rG0QGT9ICoAQ&ved=0CFAQ6AEwAw#v=onepage&q=Ethiopian%20Patronymics&f=false.  (እንግሊዝኛ)
  2. ^ Tesfagiorgis G., Mussie (2010). Eritrea. Santa Barbara, California: ABC-CLIO. pp. 236. ISBN 978-1-59884-231-9. (እንግሊዝኛ)