Jump to content

አባል:ስዩም ይዘንጋው ድንቁ

ከውክፔዲያ

ፋኖ ፋኖ ፋኖ ማለት ሳይታዘዝ በፈቃዱ ፋኖ የሚዘምት ወይም ያለ ሥራ በዘፈቀደ ዐሳብ የሚውል ውኀ ስንቁ። ፋኖ የሚዘምት ፍናኝ። በፈቃዱ ወደ ዘመቻ ከሚኼድ ጋር አብሮ የሚኼድ። -ወዶ ዘማች ፤-ፋነነ ማለት ነው ።

አገር ተወረረች በተባለ ጊዜ ሁሉ መደበኛ ስራውን ወደ ጎን በመተው “እምቢ ለሃገሬ” ብሎ ህይወቱን የሚገብር በሰላም ግዜ አራሽ ፤ በጭንቅ ጊዜ ተኳሽ ነው ። ይህ የ”እምቢ ለባርነት” የትግል አርማ የሆነው ፋኖ ከትግል መልስ አርሶአደሩ የሚያርስ፣ ነጋዴው የሚነግድና ምሁሩ ወደ መደበኛ ስራው የሚመለስ ሃይል ነው።

ፋኖ ስለሚባለው ሥያሜ ብዙ ወገኖች ግራ ሲጋቡ ይስተዋላል፡፡ ግራ መጋባቱ በተለያዬ ሰበብ ሊሆን ይችላል፡፡ አንዳንዱ ቃሉን ከነ ጽንሰ ሐሳቡ ካለማወቅ ሲሆን አንዳንዱ ደግሞ በተለዬ የፖለቲካ ዝንባሌ የተነሣ ሊሆን ይችላል፡፡ ይሄንን ነገር ለማጥራት ፋኖ የሚለውን ቃል በአጭሩ ማብራራት አስፈልጓል፡፡ ነገር ግን ይህ ጽሑፍ ወደፊት በሰፊው የሚሰናዳ ገና ጅምር ነው፡፡ ፋኖ የሚለው ቃል ከአማራ ሕዝብ ጋር በቀጥታ የተገናኘ ነው፡፡ ፋኖነት የአማራ ባህል ነው፡፡ ፋኖ አካታች ጽንሰ ሐሳብ ነው፡፡ ወንድ ወይም ሴት ወጣት ወይም ጎልማሳ ሽማግሌ ወይም አዳጊ ወጣት፣ ካህን ወይም ሸሕ፣ ክርስቲያን ወይም ሙስሊም ብሎ የሚለይ አይደለም፡፡ ሁሉም ፋኖ ነው፡፡ ፋኖ በሰላም ጊዜ እንደየሙያው ያድራል፤ የሚያርሰው ያርሳል፣ የሚቀድሰው ይቀድሳል፤ የሚነግደው ይነግዳል፤ በመንግስት መሥሪያ ያለ ሁሉ ሥራውን በዚያ ይከውናል፡፡ ሀገርን የሚወር፣ ሰንደቃላማን የሚያዋርድ፣ ሃይማኖትን የሚያረክስ ጠላት በተነሣ ጊዜ ግን በየሙያው የነበረው ይፋንናል፤ ጦሩን ሰብቆ፣ ጥሬ ሰንቆ በረሀ ይወርዳል፡፡ የተለዬ አሰልጣኝ ሳይፈልግ፣ አስታጥቁኝ፣ አልብሱኝ አጉርሱኝ ሳይል ይዘምታል፡፡ ፋኖነት ይሄ ነው፡፡