አቤ.አቤ ጉበኛ

ከውክፔዲያ


የአቤ ጉበኛ ያባትነት ግጥም…… በፍቅር አባት

አቤ ጉበኛ ሀገራችን ካፈራቻቸው ወይም ደሞ ‘’ ለሀገራቸው ራሳቸውን ካፈሩ ደራሲያን ‘’ …….. የእውነት ደራሲያን ተርታ በግንባር ቀደምትነት የሚሰለፍ ፊት አውራሪ ጠንካራ እና ተንከሽ ጠሀፊያችን መሆኑ አሌ የማንለው ሀቅ ነው ፡፡ …’’ ሳይንሳዊ ሀቅ ‘’ ነው እንበለው እንዴ! ?

ወደ አቤ ስንመለስ …. አቤ በሞገደኛ መጽሀፎቹ የጊዜውን እውነት ፍንትው አርጎ በብዕሩ የከተበ ፡፤ በእውነቱ ውስጥ እየተንቦጫረቁ ላሉ ዋናተኞች ቀዛፉዎች አስቀዛፉዎች ማንንም እና ምንም ሳይፈራ የተጠቀለሉበትን ጨለማ በመግፈፍ በሰላ የትችቱ ብርሀን ፍንትው አርጎ በመጽሀፍቱ ለአደባባይ ያበቃ ደፋር ጠሀፉም ነበር፡፡(እንዲህ እንዲህ አይነት ጠሀፊዎች በርከትከት ቢሉ ምን ነበረበት … ግን ግን ….የህይወታቸው አጨራረስ ሳይጨምር ነዋ…. )

ታዲያ በዚህም መዳፈሩ ነበር…. ዛቻውን ፡ ተግሳፁን ጠንከር ሲል ግዞቱን ሊያጣጥም የተገደደው… ግን ደሞም በዚህ ተኮላሽቶ ወደ ሁዋላው ያላፈገፈገ አቁዋሙን ሳያለዝብ ላመነበት ያለፈ የጥበብ ጀግናም ነው ፡፡ ( ህልፈቱ ያልተቁዋጨ ምስጢር ሆኖ ቢቀርም….. ማን ያውቃል ነግ ምስጢሩ ይገለጥ ይሆን ይሆናል እድሜ ለሰጠው ሰው ….)

አቤ በዘመኑ እንዲህ አይነት ቆራጥ የነበረ ቢሆንም ያው እንደ ስጋ ለባሽ ስንቃነው ፡፡ ከዚች መንደርደሪ ለጥቆ የማካፍላችሁ አጠር ያለች ግጥሙን ስናነብ ፡፡ አቤ የልጆች አባት ከሆነ በሁዋላ ልቡ የተከፈለበት ለመሆኑ አስረጅ ትሆነን ይመስለኛል …..ይመስለኛል ነው ያልኩት ……. ፍርዱን ለየራሳችን እልኩ ፡፡

ወንድነት ደከመ ወኔ ተቀነሰ ሰው ራሱ ሲሞት ለልጅ አለቀሰ ሞትን የማይፈራው ያ ቆራጡ ጀግና ልቡ ሁለት ሆነ ልጅ ከፈለውና፡፡ ለማፍሰስ የሚችል የቆራጥን አሞት የህጻናት አፍ ነው ጎልዳፋው አንደበት፡፡ ያልወለደ አረደ ሲባል ለጭከና የወለደ አይፀድቅም ተብለüል በደፈና፡፡ ወንድ ልጅ ቢደፍርም ቢጨክን በራሱ ልጅ ካለው በሁዋላ የርሱ አይደለም ነፍሱ፡፡ አባባዬ ሲሉ ማሞና ማሚቱ ሰው ለመም ይሰጋል እንካንስ ለሞቱ፡፡ ሰው መች ይደክምና ቢያስሩት በግር ብረት በልጅ ፍቅር እንጂ በብርቱ ሠንሠለት፡፡

                 በአቤ ጉበኛ  ሬትና ማር 1965 ዓ.ም ገፅ 12

,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,