Jump to content

አንበጣ

ከውክፔዲያ
አንበጣ

አንበጣ በመንጋ የመሄድ ባህሪይ ያላቸው ባለ አጭር ቀንድ ፌንጣዎች ናቸው። እነዚህ ነፍሳት የአክሪዲዴ (Acrididae) ቤተሠብ አባላቶች ናቸው። በባህሪያቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ የተመቻቸ ሁኔታ ካገኙ በብዛት መራባት የሚችሉ እና ስደተኞች ናቸው። በአጠቃላይ በከፍተኛ ጥግግት ጊዜ ቀለም ወይንም ባህሪይ የሚቀያይሩ ነፍሳቶች አንበጣ ወይንም locusts ተብለው ይጠራሉ።