Jump to content

አካድ

ከውክፔዲያ
(ከአካድ መንግሥት የተዛወረ)
የአካድ መንግሥት በታላቁ ሳርጎን ዘመን

አካድ (ሱመርኛአጋደመጽሐፍ ቅዱስአርካድ) በመስጴጦምያ የተገኘ ጥንታዊ ከተማ ነበረ። ቦታው በኤፍራጥስ ወንዝ ላይ ከሲፓርና ከኪሽ መካከል እንደ ነበር ቢታሠብም ፍርስራሹ ግን እስካሁን ድረስ አልተገኘም። ዙሪያው በሱመርኛ 'ኡሪ-ኪ' ወይም 'ኪ-ኡሪ' ተባለ።

ሱመራውያን ነገሥታት ዝርዝር መሠረት አካድ (አጋደ) የገነባው ታላቁ ሳርጎን ነበረ። ሆኖም ከተማው ከሳርጎን ቀድሞ በኡሩክ ንጉሦች ኤንሻኩሻና እና ሉጋል-ዛገሢ ዘመናት እንደተገኘ ከጽሕፈቶች ይታወቃል። በመጽሐፍ ቅዱስም (ዘፍ. 10፡10) ዘንድ ናምሩድ ከሠሩት ከተሞች 1ዱ መሆኑ ይቆጠራል። ከዚህ በላይ ኤንመርካርና የአራታ ንጉስ በተባለው ሱመራዊ አፈ ታሪክ፣ ልሣናት የተደባለቁባቸው አገሮች ሹባርሐማዚሱመር፣ ኡሪ-ኪ (የአካድ ዙሪያ) እና የማርቱ አገር በመባላቸው፤ ይህም የአካድን ጥንታዊነት ይመሰክራል። እንደገና በብዙ ጥንታዊ መዝገቦች፣ ከሰናዖር (ሱመር) ዙሪያ ሌሎቹ '4 ሩቦች' ሲዘረዘሩ እነርሱ 'ማርቱ' (አሞራውያን)፣ 'ሹባር' (አሦር?)፣ ኤላምና 'ኡሪ-ኪ' (አካድ) ናቸው።

ከአካድ ንጉሥ ከሳርጎን ዘመን ጀምሮ የአካዳዊ መንግሥት ዋና ከተማ ሆኖ ከ2077 እስከ 2010 ዓክልበ. ገደማ ገዛ። አካድኛ አንድ ሴማዊ ቋንቋ ነበርና ይህ ቋንቋ በአካዳዊ መንግሥት ጊዜ በመስጴጦምያም ሆነ በኤላም ይፋዊ ሆነ።