አኻያ

ከውክፔዲያ
ነጭ አኻያ

አኻያ (Salix) ወይም የወንዝ ዳር ዛፍዛፍ አይነት ወገን ነው።

የአኻያ ቅጠልና ልጥ ከጥንት ጀምሮ ለሕመም፣ ለትኩሳት መድሃኒታዊ እንደ ሆነ ታውቋል። በዘመናዊ ሕክምና በኩል፣ በውስጡ ያለው ጠቃሚ ውሁድ («ሳሊሲሊክ አሲድ» ወይም አኻያዊ ኮምጣጣ) ሲመረመር የአስፒሪን መነሻ ሆነ።

በአንዱ ጥናት እንደ ተዘገበ፣ የአኻያና የሰንሰል ቅጠል ጭማቂ ለሰዎችም ሆነ ለእንስሶች ውሻ በሽታን ለማከም ይሰጣል።[1]

  1. ^ የፍቼ፣ ኦሮሚያ ባህላዊ መድሃኒት ጥናት 2006 ዓም ከዓቢዩ እኒየው እና ሌሎች፣ ጎንደርና አዲስ አበባ ኡኒቨርሲቲዎች ሥነ ፍጥረት ኮሌጆች