አይሊል ማክ ስላኑል

ከውክፔዲያ

አይሊል ማክ ስላኑልአይርላንድ አፈ ታሪክ ከ803 እስከ 790 ዓክልበ. ግድም ድረስ የአየርላንድ ከፍተኛ ነጉሥ ነበር።

የአይርላንድ ታሪኮች ስለ ዘመኑ ዓመቶች ቁጥር ይለያያሉ፤ 12፣ 15 ወይም 16 ዓመታት እንደ ቆየ የሚሉ ሳሉ የላውድ አቆጣጠሮች (1014 ዓም ተቀነባብሮ) እና የድሮ አቆጣጠር በመከተል 13 ዓመታት ነበር፣ ይህ ከ803 እስከ 790 ዓክልበ. ድረስ ይሆናል። (በኋላ የታዩት ታሪኮች ግን ከዚያ በፊት ያደርጉታል።)