Jump to content

አይባ

ከውክፔዲያ
አይባ
ይባባ
የሕዝብ ብዛት
   • አጠቃላይ 3፣840
አይባ is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
አይባ

12°10′ ሰሜን ኬክሮስ እና 37°43′ ምሥራቅ ኬንትሮስ


አይባጎንደር ከተማ በስተምስራቅ በኩል 11ኪ.ሜ. ርቆ በወገራ የሚገኝ ቦታ ነው። የአካባቢው ህዝብ በገብስስንዴምርትና በግፍየል እርባታ መስኮች የተሰማራ ነው[1]። የዓፄልብነ ድንግል ሚስት እቴጌ ሰብለ ወንጌል መኖሪያዋን በአይባ አድርጋ ሳለች ከ3ዓመት በኋላ በ1537 በምርኮ ወደ የመን ተሰዶ የነበረው ልጇን ሚናስን እዚሁ ቦታ እንደተረከበች የዜና መዋዕሏ ያትታል [2]

በኋላ፣ የአጼ ሚናስ ልጅ የነበረው አጼ ሠርፀ ድንግል ለጤንነት ሲል ከጉዛራ ለቆ የአገሪቱን ዋና ከተማ በ1582 በዚሁ በአይባ መሰረተ[3]። በዚህ ቦታ ሠርጸ ድንግል ታዕካ (የቤተ መንግስት ግንብ) እና ቤተክርስቲያን አስርቶ ነበር። እንዲሁም የካቲት 28፣ 1586 ላይ ወይዘሮ ብዝግና አሕቶነ ለተባለች ሴትዮ በዚሁ ቦታ ጉልት ሰርቶላት እንደነበር ታሪክ አጥኝው ዶናልድ ክረሚ መዝግቦት ይገኛል[4]

ከዚህ በኋላ አጼ ሱሰኒዮስም የክረምት ወራትን በአይባ ያሳልፍ ነበር፣ ሆኖም በ1611 ጠቅልሎ ከተማውን ወደደንቀዝ ቀየረ [5]

ደግሞ ይዩ፦

ጉዛራ

ደንቀዝ

ጎርጎራ


  1. ^ http://www.feg-consulting.com/feg-shared-folder/liu/amhara/woreda-profiles/Gonder%20Zuria.pdf
  2. ^ Wolde Aregay, Merid: Encyclopaedia Aethiopica edited by Siegbert Uhlig Otto Harrassowitz Verlag, 2003
  3. ^ "Archive copy". Archived from the original on 2011-06-12. በ2011-05-31 የተወሰደ.
  4. ^ Donald Crummey, "Land and society in the Christian Kingdom of Ethiopia: from the thirteenth" , University of Illinois, 2000 (page 62)
  5. ^ "Archive copy". Archived from the original on 2011-06-12. በ2011-05-31 የተወሰደ.