አዲስ መዝናኛ

ከውክፔዲያ

አዲስ መዝናኛአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር መገናኛ ብዙሐን ኤጀንሲ ስር በኤፍ ኤም 96.3 ሬዲዮ ዘወትር ቅዳሜ ምሽት ከ3፡00 እስከ 6፡00 በተለይ በመረጃና ተግባቦት ቴክኖሎጂ ዙሪያ የተቀነባበሩ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ትንታኔዎችን ከሃገር ውስጥና ከውጭ ሙዚቃዎች ጋር አዋህዶ የሚያቀርብ በኢሉዥን የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሥራዎች እየተዘጋጀ የሚቀርብ የመረጃ ሰጭ መዝናኛ ፕሮግራም ነው።

አዲስ መዝናኛ ሰኔ 132001 ዓ.ም. (June 20, 2009) ተመሠረተ። ፕሮግራሙ ለሕዝብ ጆሮ ከበቃበት ዕለት አንስቶ አዘጋጅና አቅራቢዎቹ አቶ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ እና ወ/ሪት ኤዶም ካሣዬ ናቸው። የአዲስ መዝናኛ ፕሮዳክሽን ማኔጀር አቶ በፍቃዱ ኃይሉ ናቸው።

ኢሉዥን የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሥራዎች አዲስ መዝናኛን ከማስተዋወቁ በፊት በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የነበረ እና በመረጃና ተግባቦት ቴክኖሎጂ ዙሪያ የሚያጠነጥን አይሲቲ የተሰኘ የ30 ደቂቃ ሳምንታዊ የሬዲዮ ፕሮግራም በአዲስ አበባ በዛሚ ኤፍ ኤም 90.7 ላይ የሚያቀርብ የነበረ ሲሆን በሬዲዮ ጣቢያው የስርጭት ስፋት ማነስ ምክንያት ፕሮግራሙን ላልተወሰነ ጊዜ አቋርጦታል።