ኡር-ኑንጋል
Appearance
ኡር-ኑንጋል (ወይም ኡር-ሉጋል) የኡሩክ 5ኛው ንጉሥ ነበረ። በሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር ላይ 30 ዓመታት እንደ ነገሠ ይላል። ነገር ግን ከርሱ አስቀድሞ እንደ ነገሡት 4 የኡሩክ ነገሥታት (ኤንመርካር፣ ሉጋልባንዳ፣ ዱሙዚድና ጊልጋመሽ) ሳይሆን፣ በኡር-ኑንጋል ስም ምንም አፈ ታሪክ አይታወቅም። ከነገሥታት ዝርዝር በቀር ስሙ የሚጠቀሰው በቱማል ዜና መዋዕል ብቻ ሲሆን፣ የቱማል መቅደስ በኒፑር ከአባቱ ጊልጋመሽ ቀጥሎ እንደ ጠበቀው ይገልጻል።
ከኡር-ኑንጋል ዘመን በኋላ 6 ነገሥታት በኡሩክ እንደ ተከተሉ በዝርዝሩ ላይ ይላል። ነገር ግን ለነዚህ 6 ነገስታት (ኡዱል-ካላማ፣ ላባዕሹም፣ ኤን-ኑንታራህ-አና፣ መሽ-ሄ፣ መለም-አና፣ ሉጋል-ኪቱን) ምንም ቅርስ ወይም ሌላ ጥቅስ አልተገኘም። ስለዚህ ከኡር-ኑንጋል በኋላ፣ የሱመር ላዕላይነት በእውኑ ከኡሩክ ወደ ኡር ከተማ እንደ ተዛወረ ይታስባል።
ቀዳሚው ጊልጋመሽ |
የሱመር (ኒፑር) አለቃ 2350-2345 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ የዑር ንጉሥ መስ-አኔ-ፓዳ |
የኡሩክ ንጉሥ 2350-2345 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ ኡዱል-ካላማ |