ኢቤሩስ
Appearance
ኢቤሩስ ወይም ኢቤር፣ ኢቤሮ በእስፓንያ አፈ ታሪክ ዘንድ ከቶቤል በኋላ ለ37 አመት (ምናልባት 2265-2228 ዓክልበ.) የእስፓንያ 2ኛው ንጉሥ ነበረ።
ከኢቤሩስ ስም የእስፓንያ ጥንታዊ መጠሪያ «ኢቤሪያ» (Iberia) እንዳገኘው ይባላል፤ እንዲሁም ኢቤራውያን ሕዝብ ስለርሱ እንደ ተሰየሙ ተብሏል። በተጨማሪ በሮማይስጥ «ኢቤሩስ» ማለት በእስፓንያ የሚፈስሰው አሁን ኤብሮ ወንዝ የሚባለው ወንዝ ሲሆን፣ ይህ ወንዝ ስሙን ከቶቤል ልጅ ኢቤሩስ እንደተቀበለው ይታመናል። እንዲሁም ይህ ንጉሥ ኢቤሩስ በደቡብ እስፓንያ ግራናዳ ከተማ በጥንታዊ ስሙ «ኢሊቤሪስ» እንደ መሠረተው የሚል ልማድ አለ።
ቀዳሚው ቶቤል |
የኢቤሪያ ንጉሥ | ተከታይ ዩቤልዳ |