ኢናቆስ

ከውክፔዲያ

ኢናቆስግሪክ አፈ ታሪክ የውቅያኖስ እና የጤቲስ ልጅ ሲሆን የአርጎስ መጀመርያ ንጉሥ ሆነ። በአርጎስ አጠገብ የሚፈሰው ኢናቆስ ወንዝ ደግሞ ስለርሱ እንደ ተሰየመ ተባለ። ጸሃፊዎቹ ጄሮምአውሳብዮስ እንደሚሉ ኢናቆስ በሲክዮን ንጉሥ ጡሪማቆስ ዘመን የአርጎስ ንጉሥ ሆኖ ለ50 ዓመታት ነገሠ፣ ወንድ ልጁም ፎሮኔዎስ ለአርጎስ መንግሥት ተከተለው።


ጄሮም፦ «የኢናቆስ ሴት ልጅ ኢዮ ነበረች፤ ግብጻውያንም ስሟን ወደ ኢሲስ ለውጠው አመለኳት። አባትዬው ኢናቆስ በኢናቆስ ወንዝ በአርጎስ፣ ልጂቱም ኢዮ በቦስፎሮስ ወሽመት ያለውን አገር ወሰደች።»

አውሳብዮስ፦ «ከዚህ ኢናቆስ አገሩ ኢናቂያ ይባል ነበር። በሲክዮን ሰዎች 7ኛው ንጉሥ በጡሪማቆስ ዘመን፥ እርሱ የአርጎስን ሰዎች መግዛት ጀመረ።»

ፓውሳኒዩስ፦ «አሁን አርጎሊስ በተባለው አውራጃ ከሁሉ ጥንታዊ የሆነው ልማድ እንዳለው፥ ኢናቆስ ንጉሥ እየሆነ ወንዙን ለራሱ ሰየመው። በሌላ ትውፊት ግን ፎሮኔዎስ የአገሩ መጀመርያ ኗሪ ሲሆን፥ አባቱ ኢናቆስ ወንዙ እንጂ ሰው አልነበረም። ይህ ወንዝ፥ ከወንዞቹ ኬፊሶስአስቴርዮን ጋር፥ ከፖሠይዶንና ከሄራ መካከል ስለ ምድሩ ፈረዱ። ምድሩ የሄራ እንደ ነበር በየኑ፤ ስለዚህ ፖሠይዶን ውሆቻቸውን አጠፋ። ስለዚህ ነገር ኢናቆስም ሆነ ሌሎቹ የጠቀስኳቸው ወንዞች ከዝናብ በኋላ ካልሆነ በቀር ምንም ውሃ አይሰጡም።»

ቢብሊዮጤኬ፦ «ውቅያኖስና ጤቲስ ወንድ ልጅ ኢናቆስ ነበራቸው፣ ከእርሱም አንድ ወንዝ በአርጎስ ኢናቆስ ይባላል። እርሱና የውቅያኖስ ሴት ልጅ መሊያ ወንድ ልጆች ፎሮኔዎስና አይጊያሌዎስ ነበሯቸው።»


ቀዳሚው
የለም (አዲስ መንግሥት)
አርጎስ (ኢናቂያ) ንጉሥ
2149-2109 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ፎሮኔዎስ