ኣጋም
Appearance
ኣጋም (Carissa ovata) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው።
እስከ ፫ ሜትር ሊደርስ የሚችል ቊጥቋጥ ነው።
በፍጥነት ይስፋፋል። በአውስትራልያ እንደ አረም ሊቆጠር ይችላል።
በአፍሪካ፣ እስያና አውስትራልስያ ገሞጂ ይገኛል።
ትንሽ ፍሬው በሙሉ ጥቁር፣ የበሠለና ጣፋጭ ሲሆን ሊበላ ይችላል። ያልበሠለ (አረንጓዴው) ፍሬ፣ ወይም የተክሉ ፈሳሾች፣ መርዛም ናቸው።
በፍቼ ወረዳ በተዘገበ ጥናት፣ የአጋም ቡቃያ ለእባብ ነከስ ይኘካል።[1] እንዲሁም በደብረ ሊባኖስ ዙሪያ በተዘገበ ሌላ ጥናት፣ የአጋም ሥር መኘካትና ጭማቂው ለእባብ ነከስ በአፍ ይሰጣል። የአጋም ሥር፣ የጌሾ ሥርና የጫት ቅጠል አንድላይ ደግሞ ለእባብ ነከስ ይኘካል።
ወባንም ለማከም፣ የአጋም ሥር፣ የጉመሮ ሥር፣ የመናሄ ሥር፣ የጊዜዋ ሥር፣ የዱርሽት (ዱባ ሓረግ) ቅጠልና አገዶች፣ ተድቅቀው በጢስ ይናፈሳሉ።[2]
በኬንያ በሚኖር ማሳይ ብሔር መሃል፣ ተክሉ (ያልተወሰነ ክፍል) ለጡንቻና ለአንጓ ሕመም ይጠቀማል።[3]
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
- ^ የፍቼ፣ ኦሮሚያ ባህላዊ መድሃኒት ጥናት 2006 ዓም ከዓቢዩ እኒየው እና ሌሎች፣ ጎንደርና አዲስ አበባ ኡኒቨርሲቲዎች ሥነ ፍጥረት ኮሌጆች
- ^ በደብረ ሊባኖስ ዙሪያ ያለው ሕዝብ መድሃኒታዊ እጾች እውቀናና ጥቅም 1998 ዓም ከጥላሁን ተክለሃይማኖት፣ ሚሩጸ ጊዳይ፣ ግርማይ መድኅን፣ ያለም መኮነን፣ አዲስ አበባ ዩኒቬርሲቴ፣ አክሊሉ ለማ ተቋም
- ^ የኬንያ መሳይ ብሔር ባሕላዊ መድሃኒት