Jump to content

ኤክባሶስ

ከውክፔዲያ

ኤክባሶስ (ግሪክኛ፦ Έκβασος) ቢብሊዮጤኬ በሚባለው መጽሐፍ ዘንድ የአርጎስ ንጉሥ አርጉስ ልጅና ተከታይ ነበር። በአብዛኞቹ ምንጮች ግን የአርጉስ ታናሽ ልጅ ክሪያሶስ አባቱን በቀጥታ እንደ ተከተለው ሲሉ የኤባክሶስን ዘመን አይጠቅሱም።

ቢብሊዮጤኬ እንደሚለን የኤባክሶስ ልጅ አገኖር ሲሆን የአገኖርም ልጅ አርጉስ ፓኖፕቴስ ነበር።


ቀዳሚው
አርጉስ
የአርገያ (አርጎስ) ንጉሥ
1965-1915 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ክሪያሶስ