ኤውሮፕስ
Appearance
ኤውሮፕስ (ግሪክ፦ Εύρωψ) በግሪክ አፈ ታሪካዊ ዜና መዋዕል ዘንድ የሲክዮን መንግሥት ሁለተኛ ንጉሥ ነበረ። የታሪክ ጸሐፍት አፍሪካኑስ፣ ጄሮም እና አውሳብዮስ ካስቶርን (150 ዓክልበ. ግድም) ሲጠቅሱ፣ የኤውሮፕስ ዘመን 45 ዓመታት ነበረ (ምናልባት 2308-2263 ዓክልበ. ግድም)። ይህ በአሦር ንጉሥ ኒኑስ ዘመን ያሕል ነበር። ጄሮም ስለ ኤውሮፕስ አንድ አገር እንደ ተሰየመ (አውሮፓ) ይጨምራል። ፓውሳኒዩስ ደግሞ ኤውሮፕስ የአይጊያሌዎስ ልጅና የተከታዩ የቴልቂን አባት ይለዋል።
ቀዳሚው አይጊያሌዎስ |
የአይጊያሌያ (ሲክዮን) ንጉሥ | ተከታይ ቴልቂን |