ቴልቂን

ከውክፔዲያ

ቴልቂን (ግሪክ፦ Τελχίν) ወይም ቴልቂስቴልቂኔስሲክዮን ነገሥታት ዝርዝር የአርጊያሌያ (በኋላ ሲክዮን) ሦስተኛ ንጉሥ ነበር። ካስቶርን የጠቀሱት ጸሐፊዎች 20 ዓመት እንደ ነገሠ ይላሉ። ይህ ምናልባት 2263-2243 ዓክልበ. ግድም ያህል ነው። በዝርዝሩ ላይ ከኤውሮፕስ ቀጥሎና ከአፒስ በፊት ይገኛል። ፓውሳኒዩስም የኤውሮፕስ ልጅና የአፒስ አባት ይለዋል። በአርጎስ ነገሥታት ዝርዝር የአፒስ ዘመን ከዚህ በኋላ ስለሚታይ የቴልቂን ተከታይ አፒስ ሳይሆን ጤልክሲዮን ይመስላል። ሆኖም በጄሮም ዜና መዋዕል ዘንድ ይህ ቴልቂኔስ በአፒስ ዘመን ተሸንፎ ወደ ሮዶስ ሸሸ። በጥንት ቴልቂኔስ የተባለ የአረመኔ ቄሳውንት ወገን ከሮዶስ፣ ክሬታቆጵሮስ እንደ ተገኙ ይታወቅል።

ቢብሊዮጤኬ የተባለው መጽሐፍ (ከ150 ዓክልበ. በኋላ፣ በአፖሎዶሮስ ተጽፎ እንደተባለ) በፍጹም ሌላ ቅድም-ተከተል ያቀርባል። በዚህ ትውፊት ዘንድ መጀመርያው ንጉሥ አይጊያሌዎስ ያለ ልጅ ሞቶ ወንድሙ ፎሮኔዎስ አገሩን ያዘ፣ ከዚያ የፎሮኔዎስ ልጅ አፒስ አምባገነን ሆኖ አገሩን ስለ ራሱ ስም አፒያ አለው። ሆኖም ቴልቂንና ጤልክሲዮን አብረው አፒስን ገደሉት። ከዚያ በኋላ ከጊጋንቴስ ወገን (ታላላቅ ሰዎች) አርጎስ ፓኖፕቴስ ቂሙን በቅሎ ቴልቂንንና ጤልክሲዮንን ገደላቸው።

ቀዳሚው
ኤውሮፕስ
የአይጊያሌያ (ሲክዮን) ንጉሥ
2263-2243 ዓክልበ. ግድም (አፈ ታሪክ)
ተከታይ
ጤልክሲዮን