እንዳ ማርያም

ከውክፔዲያ
እንዳ ማርያም -- በአሁኑ ዘመን

እንዳ ማርያም (ቅድስት ማርያም) በቀደመው አርባዕተ አሥመራ ተብሎ በሚታውቀው መንደር አማካይ ቦታ ላይ የተሰራ ቤተክርስቲያን ነው። አርባዕተ አሥመራ በተራው የድሮውም ሆነ የአሁኑ አስመራ አማካይ ቦታ ነው።

የቀደመው እንዳ ማርያም የሂድሞ ቅርጽ የያዘ የነበር ሲሆን ግድግዳውም የደብረ ዳሞን አሰራር በሚያስታውስ-መልኩ ከድንጋይና እንጨት ንብብር የታነጸ ነበር። ይህ የጥንቱ ቤተክርስቲያን ሁለት ጊዜ የተቃጠለ ሲሆን በሁለተኛው ጊዜ ያቃጠለው ግራኝ አህመድ ነበር።

በዚህ በድሮው ቤተክርስቲያን ፈንታ አዲስ ቤተክርስቲያን በጣሊያኑ አርክቴክት ኢ ጋሎ አቅድ መሰረት 1920 ላይ ተሰራ። 1938 ላይ ከእንደገና በመታነጽ ቤተክርስቲያኑ አሁን የያዘውን ቅርጽ አገኘ።