ኦክታቭ ሚርቦ

ከውክፔዲያ
ኦክታቭ ሚርቦ (Octave Mirbeau)

ኦክታቭ ሚርቦ (Octave Mirbeau) በአውሮፓውያን አቆጣጠር ከፌብርዋሪ ፲፮ ቀን ፲፰፻፵፰ እስከ ፌብርዋሪ ፲፮ ቀን ፲፱፻፲፯ ዓመተ ምሕረት የነበረ ፈረንሣዊ ተወላጅ ሰው ነው። ይህ ሰው ጸሐፊ፣ ጋዜጠኛ፣ የኪነ ጥበብ አስተያየት ሰጭ (ሐያሲ) ከመሆኑ ሌላ የታወቀ የልብ ወለድ ደራሲ ነበር።

ኦክታቭ ሚርቦ ታጋይ ምሁር፣አናርኪስት፣ለሰላም ተከራካሪ፣የሀየማኖት ጣልቃ ገቢነትን ተቃዋሚ በመሆን ሙሉ ዕድሜውን ለሰው ልጅ መብትና ትክክለኛ ፍርድ ሲታገል የኖረ ሰው ነበር። ስለኪነ ጥበብ በተለይም ስልሰዓሊዎች ያለው አስተያየት በጊዜው ካሉት ጋዜጠኞች ቀደምንነት ስልነበረው ከሁሉም በፊት ትልቅ ማዕረግ ለማግኘት የበቁትን እነ ክሎድ ሞኔን ፣ ኦጉስት ሮደን፣ ቨነሳን ቫን ጎህ፣ ፖል ጎገን፣ ፖል ሴዛንን ለሕዝብ ማስተዋወቅ በቅቷል።

በጣም የታወቁት ሁለቱ ልብ ወለድ መጽሐፍቶቹ ፥ Le Jardin des supplices Le Journal d’une femme de chambre ይባላሉ።

እንደ አውሮውያን አቆጣጠር ፲፱፻፫ ዓ፥ም Les affaires sont les affaires ተብሎ የተጻፈው ቲያትር ድርሰት በመላው አውሮጳ በሚገኙ የቲያትር መድረኮች ላይ ትልቅ ዝነኛነትን አትርፎለታል።

ስራዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • Le Calvaire (1886)
  • L'Abbé Jules (1888).
  • Sébastien Roch (1890).
  • Le Jardin des supplices (1899).
  • Le Journal d'une femme de chambre (1900).
  • Les affaires sont les affaires (1903).
  • Farces et moralités (1904).
  • La 628-E8 (1907).
  • Le Foyer (1908).
  • Dingo (1913).
  • Combats esthétiques (1993).
  • Combats littéraires (2006).
  • Correspondance générale (2003-2005-2009).

ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]