ከርምና ፊን
Appearance
ከርምና ፊን በአይርላንድ አፈ ታሪክ ከ1149 እስከ 1109 ዓክልበ. ግድም ድረስ ከወንድሙ ሶባይርከ ጋር የአየርላንድ ጋርዮሽ ከፍተኛ ነጉሥ ነበር።
የአይርላንድ ታሪኮች እንዳሉት የከርምናና የሶባይርከ ዘመን ለ40 ዓመታት ቆየ። የላውድ አቆጣጠሮች (1014 ዓም ተቀነባብሮ) እና የድሮ አቆጣጠር በመከተል፣ ይህ ከ1149 እስከ 1109 ዓክልበ. ድረስ ይሆናል። (በኋላ የታዩት ታሪኮች ግን ከዚያ በፊት ያደርጉታል።) ከርምና በደቡቡ፣ ሶባይርከ በስሜን ሲገዙ ሁለቱ በአንድ አመት እንደ ተገደሉ ይባላል።