ኩርባ

ከውክፔዲያ

ኩርባ (slope) በሂሳብ ጥናት ያንድን መስመር የዳገት መጠን የምንለካበት ጽንሰ ሃሳብ ነው። አንድ መስመር ከፍተኛ ኩርባ አለው ስንል መስመሩ በጣም ዳገታማ ነው ማለት ነው። በአንጻሩ ዝቅተኛ ከሆነ ደልዳላ ሜዳ ነው። ኩርባው ኔጌትቭ ከሆነ ደግሞ ቁልቁለት ነው ማለት ነው።

ኩርባ በትክክል ሲተረጎም በሁለት ነጥቦች መካከል ያለውን የቁመት ልዩነት በአድማሳዊ አቀማመጣቸው ባለው ልዩንት ስናካፍል የምናገኘው ቁጥር ነው።

m - ኩርባ ነው ፣ Δy - የቁመት ልዩነት ነው፣ Δx የአድማሳዊ አቀማመት ልዩነት ነው፣ ስለዚህ m = Δyx.

በአንድ መስመር ላይ ሁለት ነጥቦች ቢሰጡን (x1,y1) and (x2,y2) የመስመሩ ኩርባ m እንደሚከተለው ነው