Jump to content

ካልቪን ኩሊጅ

ከውክፔዲያ
ካልቪን ኩሊጅ

ካልቪን ኩሊጅ (እንግሊዝኛ: Calvin Coolidge) የአሜሪካ ሠላሳኛ ፕሬዝዳንት ነበሩ። ፕረዝዳንቱ ሥልጣን ላይ የወጡት በቀዳሚው በዋረን ሃርዲንግ መሞት በ1923 እ.ኤ.አ. ሲሆን ሁለተኛ ዘመን (አራት ዓመታት) በምርጫ አገኝተው በጠቅላላ ፮ ዓመታት ገዙ። በስልጣን ዘመናቸው ምክትል ፕሬዝዳንት ሁነው የተሾሙት ቻርልስ ዳውዝ ናቸው። ፕሬዝዳንቱ የሪፐብሊካን ፓርቲ አባል የነበሩ ሲሆን የለሴ ፈርና የትንሽ መንግሥት ወዳጅ ነበሩ። ለተጨማሪ ዘመን ምርጫ ዕጩ መሆን ስላልወደዱ ከሥልጣን የወረዱት በ1929 እ.ኤ.አ. ነበር።