Jump to content

ካሞስ

ከውክፔዲያ

==

ካሞስ
የካሞስ ሬሳ ሳትን
የካሞስ ሬሳ ሳትን
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1563-1558 ዓክልበ. ግ.
ቀዳሚ ሰቀነንሬ ታዖ
ተከታይ 1 አሕሞስ
ባለቤት 2 አሖተፕ?፣
ሥርወ-መንግሥት 17ኛው ሥርወ መንግሥት
አባት ሰቀነንሬ ታዖ

==


ካሞስላይኛ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን (17ኛው ሥርወ መንግሥት) ምናልባት 1563-1558 ዓክልበ. አካባቢ በሂክሶስ ዘመን የገዛ ፈርዖን ነበረ።

ካሞስ ከብዙ ቅርሶች ከነጽላቶች ይታወቃል። በአንድ ጽላት ዘንድ በኩሽ መንግሥት ላይ እንደ ዘመተ፣ ከዚያ በ፫ኛው አመት ወይም በ1560 ዓክልበ. በሂክሶስ ላይ እንደ ዘመተ ይታወቃል። ስሜን ጠረፉን ከአቫሪስ 100 ማይል እስከ ቀረበ ድረስ አሰፋው እንጂ መላውን ታችኛ ግብጽ አልማረከም። ከዚያም በኋላ እንደገና በኩሽ ላይ ዘመተ፤ ወንድሙንም 1 አሕሞስን የጋርዮሽ ፈርዖን ሆኖ ሹሞት ነበር። ይህም አሕሞስ ሂክሶስን ከግብጽ ስላባረራቸው የአዲስ መንግሥት መስራች ይባላል።

ቀዳሚው
ሰቀነንሬ ታዖ
ግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን
1563-1558 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
1 አሕሞስ