Jump to content

የኩሽ መንግሥት

ከውክፔዲያ
(ከኩሽ መንግሥት የተዛወረ)
የኩሽ መንግሥት በሰፊነቱ ጫፍ፣ በ700 ዓክልበ. ግድም

የኩሽ መንግሥት በላይኛ አባይ ወንዝ በጥንት የተመሠረተ አፍሪካዊ መንግሥት ነበረ።

ኢትዮጵያ ታሪክ ጸሓፊዎች ዘንድ የኩሽ መንግሥት በካምና በልጁ ኩሽ ተመሠረተ። ይህ የኩሽ ወይም የኩሳ ሥርወ መንግሥት ግዛት እስከ ደጋ ድረስ ሲዘረጋ አንዳንድ ጎሣ ከውጭ አገር በተለይ ከከነዓን በዚያ ይሠፈር ነበር።

«ኩሽ» የሚለው ስም መጀመርያ በግብጽ መዝገቦች የታየው በ2 መንቱሆተፕ ዘመን ነው። ያው ፈርዖን በ2092 እና 2090 ዓክልበ. ግድም ከ2ኛው ፏፏቴ ወደ ደቡብ በኩሽ ላይ ዘመተ።

16ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. እስከ 11ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. ድረስ ኩሽ በዛሬው ሱዳን ለግብጽ አዲስ መንግሥት ተገዥ ነበር። ከዚያ እንደገና ነጻ ሆነ፣ በ8ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. የኩሽ ነገሥታት ደግሞ በግብጽ የ25ኛው ሥርወ መንግሥት ፈርዖኖች ሆኑ፤ እስከ ሶርያም ድረስ አገሩን አቀኑ።

በኢትዮጵያ ታሪክ ጸሓፊዎች ዘንድ በጥንታዊ ዘመን በኩሽ የነገሡት ገዢዎች እነዚህ ናቸው፦

  1. ካም - ከባቢሎን ግንብ ውድቀት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ገባ፣ ለ78 ዓመታት ነገሠ። ከዚያ ሶርያን በወረረበት ጊዜ ተገደለ።
  2. ኩሳ - 50 ዓመት ነገሠ።
  3. ሀባሢ - 40 ዓመት
  4. ሰብታ - 30 ዓመት
  5. ኤሌክትሮን - 30
  6. ነቢር - 30
  7. 1 አሜን - 21
  8. ንግሥት ነሕሴት ናይስ (ካሲዮኔ) - 30 ዓመት ነገሰች፤ የሲኒ ከነዓን ልጆች ወደ ኩሽ ገቡ።
  9. ሆርካም - 29 ዓመት፣ የአርዋዲ ከነዓን ልጅ አይነር ወደ ኩሽ ገባ።
  10. 1 ሳባ - 30 ዓመት፣ ዋቶ ሳምሪ ከነዓን (ፋይጦን) ወደ ኩሽ ገባ።
  11. ሶፋሪድ - 30
  12. እስከንዲ - 25
  13. ሆህይ - 35
  14. አህያጥ - 20
  15. አድጋስ - 30
  16. ላከንዱን - 25
  17. ማንቱራይ - 35
  18. ራክሁ - 30
  19. 1 ሰቢ - 30
  20. አዘጋን - 30
  21. ሱሹል አቶዛኒስ - 20
  22. 2 አሜን - 15
  23. ራመንፓህቲ - 20
  24. ዋኑና - 3 ቀን
  25. 1 ጲኦሪ - 15 አመት። የሕንድ ንጉሥ ራማ ኩሽን ወረረ፤ በኋላ የሣባ ነገሥታት በኩሽ ይገዛሉ።

ከዚህ በላይ ለዚያው ዘመን ያሕል የሥነ ቅርስ ሊቃውንት የሚከተሉትን የኩሽ (በአሁኑ ከርማሱዳን) ገዢዎች ስያሜዎች አንብበዋል፦

  • ቃካሬ ኢኒ (ስነፈር-ታዊ-ፊ)
  • ኢ-እብ-ኸንት-ሬ (ገረግ-ታዊ-ፊ)
  • ሰገርሰኒ ወይም ሰገርሰንቲ (መንኽካሬ)
  • ካዓ
  • ቴሪያሂ
  • አዋዋ
  • ኡታትረርሴስ
  • ነድጀህ