ክላሚዶሞናስ
ክላሚዶሞናስ የ አረንጓዴ ዋቅላሚዎች ወገን ሲሆን ወደ 325 ገደማ የሚጠጉ ዝርያዎች አሉት።[1] ሁሉም አንድህዋሴ ባለ ልምጭት ሲሆኑ የሚገኙትም በተኛ ውሀ ውስጥ፣ እርጥብ አፈር ውስጥ፣ ጨው አልባ ውሀማ አካላት ውስጥ፣ በባሕር ውሀ ውስጥ፣ በበረዶ ውስጥ ሁሉ ሳይቀር ነው። [2] በሞለኩላር ባዮሎጂ፣ በልምጭት እንቅስቃሴዎች ላይ በሚደረጉ ጥናቶች ውስጥ እና በዘረመል ጥናት ውስጥ እንደ ናሙና አካል በመሆን ያገለግላል። በተጨማሪም በውሃማ አካላት ውስጥ የሚገኙ መርዛማ ክቡድ ብረታ ብረቶችን ለመቀነስና ለባዮፊውል ምርት ያገለግላል።
አንድህዋሴ ህዋሳት፣ ድቡልቡል ወይም በመጠኑ በርሜሎ ቅርፅ፣ አረንጓዴ እና በአብዛኛው የኩባያ ቅርፅ ያላቸው አረንጓቀፎች፣ ቁልፍ መለያው ሁለቱ በፊትለፊት የሚገኙት ተመሳሳይ መጠን ያላቸው ልምጭቶች ናቸው።[3][4]
- ክላሚዶሞናስ አሲዶፊላ
- ክላሚዶሞናስ ግሎቦሳ
- ክላሚዶሞናስ ደብርያና
- ክላሚዶሞናስ ካውዳታ
- ክላሚዶሞናስ ኤህረንበርጊ ጎሮዣንኪን
- ክላሚዶሞናስ ኤሌጋንስ
- ክላሚዶሞናስ ሞዉሲ
- ክላሚዶሞናስ ኒቫሊስ
- ክላሚዶሞናስ ኦቮይዴ
- ክላሚዶሞናስ ራይንሓርድቲ
- ክላሚዶሞናስ ዳይሶስቶሲስ
ክላሚዶሞናስ በጨው አልባ ውሃማ አካላትና በእርጥበታማ አፈር ውስጥ በስፋት ተሰራጭቶ ይገኛል። በአጠቃላይ በአሉሚንየም በበለፀግ ምቹጌ ውስጥ ይገኛል። ለብርሃን ትብትነት የሚያግለግሉ ቀያይ የአይን ነጠብጣቦች ሲኖሩት በፆታዊ እና ኢፆታዊ መራቦ ይራባል። የክላሚዶሞናስ ኢፆታዊ መራቦ በዙስፖሮች፣ አፕላኖስፖሮች፣ ሃይፕኖስፖሮች ወይም ፓልሜላ ደረጃ[5] አማካኝነት ሲከናውን ፆታዊ መራቦው ደግሞ በአይሶጋሚ፣ አናይሶጋሚ ወይም ኦኦጋሚ አማካኝነት ይከናወናል።
አብዛኛዎቹ ዝርያዎች የግድ በብርሃናዊ አስተፃምሮ ምግባቸውን ማዘጋጀት ሲኖርባቸው፣ ክላሚዶሞናስ ራይንሓርድቲ እና ክላሚዶሞናስ ዳይሶስቶሲስ በጨለማ ውስጥ ቢሆኑ እንኳን አሲቴት ካለ እሱን እንደ ካርቦን ምንጭ በመጠቀም ምግባቸውን ማዘጋጀት ይችላሉ።
- ተንቀሳቃሽ አንድህዋሴ ዋቅላሚ
- በአጠቃላይ ሞላላ ቅርፅ ያለው
- ህዋስ ግንቡ የተዋቀረው ከሴሉሎስ ሳይሆን ከግላይኮፕሮቲንና ከኢሴሉሎሳዊ ፖሊሳካራይድ ነው።
- ተኮምታሪ ፊኝቶች የሚገኙት ከልምጭቶች መሰረት አጠገብ ነው።
- ሁለት ልምጭቶች አሉት።
- ኩባያ ወይም ጎድጓዳ ሳህን የመሰል አረንጓቀፍ በውስጡ ይገኛል
- ^ Smith, G.M. 1955 Cryptogamic Botany Volume 1. Algae and Fungi McGraw-Hill Book Company Inc
- ^ Hoham, R.W., Bonome, T.A., Martin, C.W. and Leebens-mack, J.H. 2002. A combined 18S rDNA and rbcL phylogenetic analysis of Chloromonas and Chlamydomonas (Chlorophyceae, Volvocales ) emphasizing snow and other cold-temperature habitats. Journal of Phycology, 38: 1051–1064
- ^ Harris, Elizabeth H. ( 2009) "The Genus Chlamydomonas" In The Chlamydomonas Sourcebook (Second Edition), chapter 1, volume 1, pages 1-24. ISBN 9780080919553 doi:10.1016/B978-0-12-370873-1.00001-0
- ^ Guiry, M.D., John, D.M. Rindi, F. and McCarthy, T.K. (ed) 2007 New Survey of Clare Island Volume 6: The Freshwater and Terrestrial Algae. Royal Irish Academy. ISBN 978-1-904890-31-7
- ^ "Life Cycle of Chlamydomonas (With Diagram)". BiologyDiscussion.com. 2016-09-16. Retrieved 12 March 2018.