ክላይቭ ሉዊስ
Appearance
ክላይቭ ስተይፕልዝ ሉዊስ ወይም በተለመደ እንደሚታወቅ ሲ. ኤስ. ሉዊስ (እንግሊዝኛ፦ C. S. Lewis) (1891-1955 ዓም) የብሪታንያ (አየርላንድ) ጸሐፊ ነበር።
ብዙ ጽሑፎቹ የክርስትና ሃይማኖት ምሳሌዎች ተብለዋል። ከሥራዎቹ በተለይ ዝነኛ የሆኑት «የናርኒያ ዜና መዋዕሎች» የተባሉት ልብ ወለዶች ናቸው። በታሪኩ አራት ልጆች ከዚህ አለም ወደ ሌላ ሕልም አለም በትንግርት ተሸጋገሩ። የአምላክ ክርስቶስ ትስብዕት ወደዚያውም አለም ሲጎበኝ፣ ትስብዕቱ «አስላን» የተባለ አንበሳ ነው። (ስሙም «አስላን» በቱርክኛ አንበሳ ማለት ነው። )