ክብሪት

ከውክፔዲያ
ክብሪት በላይተር ሲቀጣጠል

ክብሪት እሳትን በፈለግነው ጊዜ ለማግኘት የሚጠቅመን መሳሪያ ነው። ሁለት የክብሪት ዓይነቶች ሲኖሩ አንደኛው ደህንነት ክብሪት ሲባል እሳት የሚፈጥረው ለዚሁ ተግባር ብቻ ተብሎ ከተሰራ ገጽ ላይ ሲጫር ነው። ሁለተኛው አይነት ሁሉ ቦታ ጫሪ ሲባል የትም ሸካራ ቦታ ላይ ሲጫር ቦግ ብሎ ይቃጠላል።

የክብሪት እራስ ድሮ ድሮ ከድኝ የሚሰራ የነበር ሲሆን አሁን ግን ከፎስፎረስ ወይም P4S3ፎስፎረስ ሴስኩዊሰልፋይድ (ሁሉ ቦታ ጫሪ) ና ይህን ኬሚካል ከእንጨቱ ጋር ከሚያጣብቅ ሙጫ ነው።