ወሓካ ዴ ዋሬዝ
Appearance
ወሓከ ዴ ዋሬዝ (እስፓንኛ፦ Oaxaca de Juárez) የወሓካ፣ ሜክሲኮ ከተማ ነው። ኋሽያካክ ተብሎ የተመሠረተው በ1432 ዓ.ም. በአዝቴክ (መሺካ) ኗሪዎች ነበር። በ1514 ዓ.ም. ስፓኒሾች ደርሰው ጓሓካ አሉት፣ በ1521 ዓ.ም. ግን ስሙ አንቴኬራ ሆነ። በ1813 ዓ.ም. ሜክሲኮ ከእስፓንያ ነጻነቱን እንዳገኘው እንደገና «ወሓካ» ተባለ። በ1864 ዓ.ም. የከተማው ኗሪ ቤኒቶ ዋሬዝን ለማክበር ዴ ዋሬዝ ወደ ስያሜው ተጨመረ።
የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር የአካባቢውን ኗሪ ሲጨምር 3,801,962 ሆኖ ሲገመት የራሱ የከተማው ኗሪ ቁጥር ደግሞ 93,952 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 18°39′ ሰሜን ኬክሮስ እና 93°52′ ምዕራብ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።