ወይራ
Appearance
ወይራ (Olea europaea) በአለም ዙሪያ የሚገኝ ዛፍ ተክል ነው።
በግዕዝ እንዲሁም በአረብኛ እና በእብራይስጥ ዛፉ «ዘይት» ተብሏል፤ ይህም በአማርኛ «ዘይት» የሚለው ቃል መነሻ ነው።
ከቅድመ-ታሪክ ጀምሮ በሜድትራኔያን ባህር ዙሪያ ታርሷል፤ አሁንም በብዙ አገራት ይታድጋል። በተለይ በሞቀ አገር ለባህር ወይም ውቅያኖስ ቅርብ በሆነ ቦታ ይበቅላል።
ከፍራፍሬው ጭምር የወይራ ምርቶች የወይራ ዘይትና እንጨት ናቸው። የወይራ ቅጠልም በአንዳንድ ባሕላዊ መድሃኒት ውስጥ ይጠቀማል።
በባሕል መድሃኒት፣ የወይራ ዘይት መረቅ ጠብታ በጆሮ ለጆሮ ሕመም ተዘግቧል።[1]
አደገኛ ዝርዮች፦
- የወይራ ትንኝ - ዕንቁላል በፍሬው ታስቀምጣለች
- Cycloconium oleaginum ፈንገስ
- Pseudomonas savastanoi ባክቴሪያ
- አንዳንድ አባጨጓሬ ቅጠሉን አባባንም ይበላል
- ጥቁሩ የቅርፊት ሦስት አጽቄ
- የእንኮይ ነቀዝ ቅጠሉን ይበላል
- ጥንቸል ልጡን ይበላል።
- ትንሽ አይጥ ወይም ትንንሽ ዘራይጥ ሥሩን ይበላል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
- ^ በደብረ ሊባኖስ ዙሪያ ያለው ሕዝብ መድሃኒታዊ እጾች እውቀናና ጥቅም 1998 ዓም ከጥላሁን ተክለሃይማኖት፣ ሚሩጸ ጊዳይ፣ ግርማይ መድኅን፣ ያለም መኮነን፣ አዲስ አበባ ዩኒቬርሲቴ፣ አክሊሉ ለማ ተቋም