Jump to content

ውክፔዲያ:ብልግና

ከውክፔዲያ
  • 1. ይህ አማርኛ ዊኪፔድያ በተለይ የሚጠቀመ አማርኛ ለሚችሉ ሰዎች ሲሆን፤
  • 2. አማርኛ ከሚችሉት ሰዎች መካከል አብዛኛው በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፤
  • 3. በኢትዮጵያ ውስጥ ወሲብ ነክ ብልግና (ፖርኖግራፊ) ሕገ ወጥ በመሆኑ መጠን ሁሉ፤

ስለዚህ፦

  • 1. በዚህ ውክፔድያ ላይ የብልግና ስዕል አይፈቀደም።
  • 2. በዚሁ ውክፔድያ ላይ ወደ ብልግና የሚወስድ የውጭ መያያዣ አይፈቀደም።
  • 3. እንደ ኢትዮጵያ ሕገጋት የሕዝቡን መልካም ጸባይ የሚያውክ ነገር ወይም ጉዳይ ሁሉ ክልክል ይሆናል። ይሁንና ሆን ብሎ ወሲባዊ ስሜት ወይም ፍትወት ብቻ ለማስገኘት የማይታስበው ሥነ ጥበባዊ፣ ሥነ ጽሑፋዊ ወይም ሳይንሳዊ ጸባይ ያለው መረጃ ይፈቀዳል።

ቅጣቶች

በኢትዮጵያ 1996 ዓ.ም. መቅጫ ሕግ (ወንጀላዊ ፍትሕ) መሠረት ወሲብ ነክ ጽሑፍ ሁሉ አጥብቆ ስለሚከለከል ይህን ሕግ የሚጥስ ሰው ከ6 ወር እስከ 3 አመት ድረስ በቀላል መታሰር ሊቀጣ ይችላል። ከዚህ በላይ ከ10 እስከ 10,000 ብር የገንዘብ መቀጮ ይሆንበታል። ከባድ በሆነ ሁኔታ ግን (ለምሳሌ ሰው በየጊዜው የሚነግድበት ሲሆን) መታሰሩ ቢያንስ 1 አመት ይሆናል። (ርዕስ አራት «በመልካም ጠባይ እና በቤተዘመድ ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች»)

ከዚህ ቀድሞ በ1949 ዓ.ም. በአጼ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በወጣ መቅጫ ፍትሕ መሠረት ግን ይህ አይነት ብልግና እንደ ዛሬ ክልክል ቢሆንም ቅጣቱ ግን ከአሁን ያንስ ነበር። ከዚያ ዘመን እስከ 1996 ድረስ ቅጣቱ እንደ ከባድነቱ መጠን ከ10 ቀን ወይም $1 ብቻ አንሥቶ እስከ 3 አመት ወይም $5000 ድረስ ነው።[1] (pdf)

ከ1914 ዓ.ም. በፊት ደግሞ፣ በፍትሐ ነገሥት መሠረት ለዝሙት ያባባለ ሰው አፍንጫው ሊቆረጥ ይቻል ነበር።

እዚህ በውክፔድያ ላይ ሰውን ማሰር ወይም ማስከፈል አይቻልም። ዳሩ ግን ከላይ የተዘረዝሩት ደንቦች የሚጥሰውን -- ማለት የመዝገበ ዕውቀቱን መልካም ጸባይ የሚያውከውን ሁሉ -- ማገድ ይቻላል። ማገድ የሚደረገው በማንኛውም መጋቢ ነው። ስለዚህ የቅጣቱ (የማገጃው) ግዜ እንደ 1949 ዓ.ም. ፍትሕ በከባድነቱ መጠን ከ10 ቀን ጀምሮ ይሆናል። በመዳገም የሚያደርገውም ከ1 ወር ጀምሮ ይታገዳል። መጋቢው ደግሞ ጽሑፉን በፍጥነት እንዲያጠፋ ይገባል።