ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ሐምሌ 16
Appearance
- ፲፱፻፳፩ ዓ/ም - የኢጣልያ የፋሽስት መንግሥት የሌላ ቋንቋ ወይም ባዕድ ቃላትን መጠቀምን ሕገ-ወጥ አድርጎ ደነገገ። (ኢትዮጵያም እንዲህ አይነት ህግ ባወጣች!!!!)
- ፲፱፻፵፬ ዓ/ም - በጋማል አብደል ናስር የተመሠረተው የግብጽ የመኮንኖች እንቅስቃሴ በ ጄነራል ሙሐመድ ናጊብ መሪነት ንጉሥ ፋሩቅን ገለበጠ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የግሪክ ወታደራዊ መንግሥት ውድቅ ሆኖ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር ኮንስታንቲን ካራማንሊስ መንግሥት እንዲመሠርቱ ተጋበዙ።
- ፲፱፻፺፩ ዓ/ም - የሞሮኮው አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን አል ሓሳን አባታቸው ንጉሥ ዳግማዊ ሀሰን በተወለዱ በ ሰባ ዓመታቸው ሲሞቱ ንጉሥ ሞሐመድ አራተኛ ተብለው የንጉሥነት ዘውድ ጭነው ነገሡ።