ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ሚያዝያ 11
Appearance
- ፲፮፻፹፰ ዓ/ም - የሆሣዕና በዓል ማግሥት የኢትዮጵያ ርዕሰ ከተማ በነበረችው በጎንደር ከተማ በአንዲት ሴት-አዳሪ ቤት የተነሳ እሳት በ’ግራ ቤት’ አካባቢ ያሉትን ቤቶች በሙሉ ከመፍጀቱም ባሻገር፤ የቅዱስ ጊዮርጊስ፣ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት እና የኢየሱስ አብያተ ክርስቲያናትም ተቃጥለዋል።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ የአብዮት እንቅስቃሴ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ልጅ እንዳልካቸው መኮንን የፖሊስ ሠራዊት አባላትን አነጋገሩ። በዚሁ ዕለት የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር አክሊሉ ኃብቴ ሥራቸውን ለቀቁ።