ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ሰኔ 5

ከውክፔዲያ
  • ፲፯፻፸፭ ዓ/ም - በቻይና የሲቹዋን ግዛት ውስጥ ከአሥር ቀናት በፊት የተከሰተው የመሬት እንቅጥቅጥ ምክንያት በድንጋይና አፈር ናዳ ተገድቦ የነበረው ‘ዳዱ’ የተባለው ወንዝ ይሄንኑ ግድብ ጥሶ ሲሄድ መቶ ሺ ያህል ሰዎች በጎርፉ ተጥለቅልቀው ሞተዋል።
  • ፲፱፻፸፱ ዓ/ም - የመካከለኛው አፍሪቃ ሪፑብሊክ የቀድሞው አምባ-ገነን ‘ቄሳር’፣ ዣን ቤደል ቦካሳ በአሥራ ሦስት ዓመት የሥልጣን ዘመናቸው ጊዜያት ለፈጸሟቸው ወንጀሎች የሞት ቅጣት ተፈረደባቸው።