ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ኅዳር 9
Appearance
- ፲፬፻፹፮ ዓ.ም. ክሪስቶፎሮ ኮሎምቦ የተባለው ኢጣልያዊ መርከበኛ በሰሜናዊ አሜሪካ ምሥራቃዊ ድንበር በአትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ የምትገኘውን የፑዌርቶ ሪኮ ደሴትን አገኘ።
- ፲፱፻፲፩ ዓ.ም. በባልቲክ ባሕር የምትገኘው ላትቪያ ከሩስያ ነጻ የሆነች ሉዐላዊ አገር መሆኗን አወጀች።
- ፲፱፻፲፱ ዓ.ም. በደብሊን አየርላንድ የተወለደው ታዋቂ የሥነ ጽሑፍ ሰው ጆርጅ በርናርድ ሾው የተሸለመውን ኖቤል ቢቀበልም ለዚሁ ሽልማት የተወሰነውን 118,165 የስዌድ ክሮና ግን አልቀበልም አለ። በኋላ ግን በገንዘቡ በስዌድ ቋንቋ የተጻፉ መጻሕፍት ወደ እንግሊዝኛ እንዲተረጎሙበት አደርገ። ጆርጅ በርናርድ ሾው የሽልማቱ አሸናፊነቱ ይፋ በሆነ ጊዜ፤ “አልፍሬድ ኖቤል ዲናሚት መፍጠሩን ይቅር ልለው እችላለሁ፤ ነገር ግን የኖቤል ሽልማትን ለመፍጠረ የሚበቃ ግን በሰው የተመሰለ ሰይጣናዊ መንፈስ ነው” አለ።
- ፲፱፻፵፱ ዓ/ም - ልዑል ራስ ካሣ ኃይሉ በዚህ ዕለት በሞት ተለዩ።
- ፲፱፻፷፱ ዓ.ም. የእስፓኝ የሕዝብ ምክር ቤት፣ አገሪቱን ከ ሠላሳ ሰባት ዓመት የ”አምባገነን” መንግሥት ስርዐት በኋላ፣ ወደዴሞክራሲያዊ ስርዐት የሚያሸጋግር ህግ አጸደቀ።