ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/የካቲት 12

ከውክፔዲያ

የካቲት ፲፪

  • ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - ለኢጣሊያ ንጉሣዊ ቤተሰብ አንድ ልዑል በመወለዱ ምክንያት በጄነራል ግራዚያኒ ትዕዛዝ በቀድሞው የገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት (የአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቅጽር ግቢ ከተሰበሰቡት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፤ ለፋሺስቶቹ ያደሩ ከሀዲ ባንዳዎችና መኳንንት፤ የፋሺስት ባለ ሥልጣናት ወታደሮች በተሰበሰቡበት መኻል፣ አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም የእጅ ቦምብ ወርውረው አደጋ ሲጥሉ ግራዚያኒን ጨምሮ ብዙ ሰዎች ተጎድተዋል። ይኸንን ድርጊት በመበቀል ሰበብ እዚያው ግቢ ውስጥ ከሶስት መቶ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ተጨፈጨፉ፤ ቀጥሎም የተማሩ ወጣቶች፣ የጦር መኮንኖችና ካህናት፣ የደብረ ሊባኖስ መነኮሳት በሙሉ እየተለቀሙ ተጨፈጨፉ። የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን በቤት ውስጥ እያስገቡ ከውጭ ቆልፈው ቤንዚን እያርከፈከፉ አቃጠሉአቸው። በአካፋ፣ በዶማ፣ በመጥረቢያ በተገኙበት ኢትዮጵያውያንን እየቆራረጡ የደም ጎርፍ አወረዱ። ፋሽስቶች የአዲስ አበባንና የአካባቢውን ሕዝብ በጅምላ ጨፈጨፉት። በሶስት ቀናት ፴ሺህ ሕዝብ መስዋዕትነት ተቀበለ።
  • ፲፱፻፸፩ ዓ/ም - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኢቲ-ኤ-ኤፍ ደብልዩ (ET-AFW) ዲሲ ፫ (Douglas C-47B-10-DK፤ በደቡብ-ምዕራብ ኤርትራ በምትገኘው ባረንቱ ላይ በቦምብ ፍንዳታ ተከስክሶ ሲወድቅ አምስቱም ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል። አየር ዠበቡም ከጥቅም ውጭ ሆኗል።
  • ፲፱፻፹፱ ዓ/ም - የአዲሲቷን ቻይና የሰብዓዊ እና ኤኮኖሚካዊ ገጽታዎች በማነጽ አገሪቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ አሁን የያዘችውን የኤኮኖሚያዊ ኃያልነት ሥፍራ እንድትይዝ ያስቻሏት መሪዋ ዶንግ ዥያው ፒንግ በተወለዱ በ ፺፪ ዓመታቸው አረፉ።