ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/የካቲት 24
Appearance
- ፲፱፻፪ ዓ/ም - እቴጌ ጣይቱ ብጡል ከሥልጣን ከመውረዳቸው ከሁለት ሣምንት በፊት፣ ለመጨረሻ ጊዜ በዚህ ዕለት ከሰጡት ሹመቶች አንዱ፣ የሐረርጌን ጠቅላይ ገዥነት ለደጃዝማች ተፈሪ መኮንን (በኋላ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ) ነው።
- ፲፱፻፲ ዓ/ም - የቤጌምድር እና የስሜን ንጉሥ ወልደ ጊዮርጊስ ደብረ ታቦር ላይ አርፈው እዚያው ተቀበሩ።
- ፲፱፻፳፯ ዓ/ም - የዐቢይ ጾም ቅበላ ዕለት ዓፄ ኃይለ ሥላሴ መምህር ገብረ ጊዮርጊስን (በኋላ አቡነ ባስልዮስ) እጨጌነት ሾሟቸው።