ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/የካቲት 3
Appearance
- ፲፯፻፰ ዓ/ም - በእስራት ላይ የነበሩት የ ፳፩ ዓመቱ ጎልማሳና የንጉሥ ኢያሱ አድያም ሰገድ ልጅ ዳግማዊ ዓፄ ዳዊት እንደነገሡ አዋጅ ተነገረ።
- ፲፰፻፵፯ ዓ/ም - ደጃዝማች ካሳ (ዓፄ ቴዎድሮስ)ና ደጃዝማች ውቤ ቧሂት ላይ ድንኳን ተክለው ተገናኙ። ደጃዝማች ካሳም የእንግሊዙን ሊቀ መኳስ ዮሐንስን (John Bell)በመንጥር አይተህ ንገረኝ አሉት። የሸማ ድንኳን ባየ ጊዜ ነገራቸው። ደጃዝማች ካሳም «አያሳድረኝ አላሳድረውም» ብለው ተናገሩ። ያንግዜውንም ተነሣ አሉ። ባሰለፉትም ጊዜ እንዴህ ብለው በፍከራ ትንቢት ተናገሩ። «እንኳን ይህን ቁርጥማታም ወሎን፣ መትቼ የሻዋውን ንጉሥ እይዘዋለሁ። ስሜን ስሜን እንግርሀለሁ ያልሁህ ወታደር ስሜም ቴዎድሮስ ነው» አሉ። አስቀድሞ ገና በንጉሥ አምላክ በል። ስሜን ስሜን እነግርሀለሁ ብለው ነበርና። ያንጊዜውን እንዴህ አሉ። «ወታደር አይዞህ አትፍራ። የውቤ ነፍጥ የውቤ ነፍጥ ቢልህ የተለጎመው ጨርቅና ባሩድ ነው። አይነካህም» አሉት። እኔ የክርስቶስ በርያ ሁሉንም አሳይሀለሁ ወታደር ባሉ ጊዜ ሰልፍ ገጠመ። ደጃች ውቤም ተያዙ።