ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ጥር 29
Appearance
- ፲፯፻፷፯ ዓ/ም - የሸዋው መስፍን መርዕድ አዝማች አምኃ ኢየሱስ፣ ሐር-አምባን እንደ እልፍኝ፤ አንኮበርን እንድ አዳራሽ አድርገው ለ፴፬ ዓመታት ከገዙ በኋላ አርፈው እሳቸው ባሠሩት የአንኮበር ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ተቀበሩ። ልጃቸው መርዕድ አዝማች አስፋ ወሰን ተተክተው የሸዋ መስፍን ሆኑ።
- ፲፰፻፸፯ ዓ/ም - ካይሚ የተባለ የጣልያን የባህር ኃይል መኮንን ምጽዋ ወደብን ይዞ የአገሩን ሰንደቅ ዓላማ ካውለበለበ በኋላ፣ የግብጽ እና የብሪታኒያ መንግሥቶች ወደቡን እንድይዘው ፈቅደውልኛል ብሎ አወጀ።
- ፲፱፻፴፯ ዓ/ም - ዝነኛው የሬጌ ሙዚቀኛ ሮበርት ኔስታ ማርሊ ተወለደ።