ውክፔዲያ ውይይት:የአርዕስትና የስም አጻጻፍ ልምድ

Page contents not supported in other languages.
ከውክፔዲያ

ሰላም፣

ስለ ኤድስ ያስቀመጥኩትን የሚያነሳው ማነው? መጨመር ኣይሻልም?

ኣመሰግናለሁ!


ሰላም::

ጥያቄዎች አሉኝ::

  • "የዘመን አቆጣጠር ሥርዐት" ላይ: December 26, 2005 እንደምሣሌ ቀርቧል:: ወሩን በላቲን ፊደሎች መጻፍ ይሻላል ወይስ በግዕዝ ፊደላት?
  • ብዜት ላይ የግዕዝ ነው ወይስ የአማርኛ የአረባብ ዘዴን መከተል ያለብኝ?
  • "የክፍለ ሀገር ስም ከሆነ - ስሙን ከዚያም ኮማ እና አንድ ባዶ ቦታ(space) እና የሀገሩ ስም" ይላል:: ኮማ ይሻላል ወይስ ነጠላ ሰረዝ?

አንድ አጠቃላይ አስተያየት አለኝ:: በተቻለ መጠን ግልጽ እና የማያሻሙ የአሰፘር ዘዴዎችን ማውጣቱ በኋላ እነሱን ለማረም ከመድከም የሚሻል ይመስለኛል::

ከምስጋና ጋር

--ሀሁ


ጤና ይስጥልኝ

  1. 'December' የእንግሊዝኛ ወር ስም ስለሆነ በላቲን ዓልፋቤት ቢጻፍ ስኅተት አይመስለኝም። ይሁንና ብዙ ጊዜ ቃሉ በፊደል እንደ 'ዲሤምበር' በሚመሥል አጻጻፍ ታይቷል። የወሮች ስም በሌሎቹ ቋንቋዎች ሌላ አጠራር እንዳላቸው ይታወሳል - በፈረንሳይኛ Décembre ዴሳም ይሰማል፣ በእስፓንኛም Diciembre ዲስየምብሬ ይባላል። የውጭ አገር ቃላት በላቲን አልፋቤት ሲሆኑ አንዳንዴ ቀጥታ በፊደል መካከል እንደዚያ መታየታቸው የተለመደ ሲሆን አንዳንዴ ደግሞ አጠራሩ እርግጥ ቢታወቅ ወደ ፊደል መልክ ተለውጠው ተገኝተዋል። ስለዚህ ሁለቱ ዘዴዎች ተቀባይነት አላቸው።
    ለመሆኑ በዚህ ጠቅላላ ፕሮጀክት interface ላይ የጎርጎርዮስ ወሮች ሁሉም ቦታ (ለምሳሌ በ'ቅርብ ለውጦች' ላይ) ወደ ኢትዮጵያ ወሮች መቀየር ባይቻለኝም (ቀኖች በቁጥር ስለሚለያዩ) የእንግሊዝኛ ወር ስም ግን ወደ ፊደል (እንደ 'ዲሴምበር') በቀላል መቀየር እችላለሁ። ይህ ዘዴ በአማርኛ ውክሽኔሪ አሁን በከፊል ይጠቀማል እዚህም ሊደረግ ይቻላል ምን ታስባላችሁ?
  2. መጣጥፍ ውስጥ፣ ወይም የግዕዝ ወይም የአማርኛ ብዙ ቁጥር አይነት ይፈቀዳል። ሁለቱ ትክክለኛ ናቸው። ሁለቱ በአንዱ ቃል ላይ (ለምሳሌ፣ 'ቃላቶች') ግን ከቶ አይገባም! በአርዕስት ግን፣ ከተቻለ ነጠላ ቁጥር ይመረጣል።
  3. በኔ አስተያየት ሰረዝ (፣) ከኮማ ለአማርኛ አርዕስት በጣም ይሻላል። ይህ ክፍል በእልፍአለም (ሌላው ሳይሶፕ) ስለ ተጻፍ ግን ጥልቅ ማለት አልወደድኩም! እሱን ጠይቀን ምናልባት ልናሻሽለው ብንችል እናያለን...!

በጠቅላላ በማንኛውም ገጽ ላይ እዚህ ሳይቀር ማዘጋጀትና ማረም ለሰው ሁሉ ይፈቀዳል!

ይህ ሁሉ የኔ እይታ ነው፤ የኔ ውልደት ቋንቋ ነው ለማለት ስለማልችል ግን እንዴት እንደሚመስሎ ማወቅ እወዳለሁ! ከክብር ጋር፣ --ፈቃደ (ውይይት) 01:13, 3 June 2006 (UTC)

ስለ ሆህያት[ኮድ አርም]

(ከተፈለጉ ፅሑፎች ተዛውሮ፦)

ዊኪ ላይ በዓማርኛ ሲጻፍ የምንጠቀመው በተቀነሱት ፊደላት ነው ወይንስ በትክክለኞቹ ሆህያት? ምሳሌ - "ሥራ" ወይስ "ስራ"? User:ኣብሻ

«ሥራ» ለግዕዝ አጻጻፍ ትክክለኛ ቢሆንም በአማርኛም የተሻለ ወይም የተመረጠ ቢሆንም፣ «ስራ» እንደ ስኅተት እንደሚቆጠር አይመስለኝም። ሁለቱ ሲፈራረቁ ብዙ ጊዜ በተከበሩ ህትመቶችም ሲታዩ ተራ ነገር ነው። ስለዚህ አዛጋጆች እዚህ ሲጽፉ፣ ሁለታቸውን የምንቀብል ብንሆን እንደሚሻል እገምታለሁ። ነገር ግን አንድ ቃል ወደ ተሻለው ወይም ወደ ተመረጠው ወይም ወደ ግዕዙ አጻጻፍ ለማስተካከል የሚፈልግ አዛጋጅ ቢኖር ይህ ደግሞ መልካም ነው። ለመሆኑ ለመጣጥፉ አርዕስት ከአንዱ ወደ ሌላው አጻጻፍ መምሪያ መንገድ ለመፍጠር ቀላል ነገር ነው! ፈቃደ (ውይይት) 14:25, 10 ፌብሩዌሪ 2008 (UTC)[reply]

ፈቃደ፣ በተቻለ መጠን የአማርኛ ቃላት በትክክለኛ ፊደላት መጻፍ ይኖርባቸዋል። በእርግጥ ለአንዳንዶቻችን ለቃላት የትኛውን ፊደል በትክክል መምረጥ ያስቸግራል። ሆኖም ለምሣሌ በ"ፀሐይ" ፋንታ "ጸሀይ" ወይም በ"ዓለም" ፋንታ "አለም" ወይም በ"ንጉሥ" ፋንታ "ንጉስ" ፣ ወዘተረፈ፣ ሆኖ ሲጻፍ ለአንባቢ ዓይን እና መንፈስ አጸያፊ ነው። ትክክለኛ ፊደላትን መጠቀም ደግሞ "ለግዕዝ አጻጻፍ" ብቻ ወይም "በአማርኛም የተሻለ ወይም የተመረጠ" ብቻ ሳይሆን ትክክለኛም ነው። አንተ ፊደላት "ሲፈራረቁ ብዙ ጊዜ በተከበሩ ህትመቶችም ሲታዩ ተራ ነገር ነው" ብለሃል። በእኔ አስተያየት ግን ዊኪፔድያ ላይም ሆነ በሌላ ጽሑፍ መልክ የግዕዝ ፊደላችንን ማጠንከር እንጂ በቸልተኝነት'ማ እነዚያ 'የተከበሩ' ያልካቸው የጀመሩትን የቋንቋ አዳካሚነት መንገድ መከተል ነው። ባይሆን የአጻጻፉን ስልት እና የትክክለኛ ፊደላትን አጠቃቀም፣ የቋንቋው ጽሑፍ ሊቃውንት በዊኪ ርዕስ ቢጽፉልን እጅግ መልካም ጥቅም ይሰጠናል።--Bulgew1 10:26, 26 ኤይፕርል 2008 (UTC)

ስለ ሀ እና አ[ኮድ አርም]

በኣማርኛ የ"ሀ" እና የ"ሃ" እንዲሁም የ"አ" እና የ"ኣ" ድምጾች ኣንድ የሆኑት በስህተት ይመስላል። የ"ሀ" ድምጽ ኣሁን በስህተት ለ"ኸ" ብቻ የምንጠቀመው፣ እንዲሁም የ"አ" ድምጽ ኣሁን በስህተት ለ"ኧ" የምንጠቀመው ነው የምንል ኣለን። ተሳስተናል?

```` አዎን! ተሳስታችኋል። ተሳስታችኋል ሰልም፣ በቀላሉ መልስ የሚያሰጥም ጥያቄ ነው ማለትም አይደለም። እንደነገሩ፣ አንዳንድ ጥያቄዎች በቀጣዩ መልስን ከመጋበዝ ይልቅ፣ እራሳቸው ደግመው ጥያቄ የማስነሳት ባህራይ አላቸው። “ተሳስተናል፧” ጥያቄ ከሚያጨርሩት ወገን ነውና፣ የሚከተሉትን ጥያቄዎች እንመልከት።

፩ኛ/ የአማርኛ ቋንቋ የበላይ ጠባቂው ማን ነው፧ ስርአትና ደንብ የማውጣት እና(ያለ ወይም ካለ ግዴታ) በጠቃሚ መልኩ፣ ልምዱ ተቀላጥፎ ልምዱን እስከ ወዲያኛው የሚያዘልቀው፣ በድጋሚ ማን ነው፧
፪ኛ/ አማርኛ ቋንቋው፣ ከጅምሩ የራሱን የፊደል ገበታ እስካልፈጠረ ወይም እሰከሌለው ድረስ፣ በተውሶ የሚጠቀምበት የግእዝ ፊደላት፣ ሙሉ ስፌት( ልክክ) ብሎለታል ወይ፧ ግእዝ ቋንቋ እራሱስ፣ የግዕዝን የፊደል ገበታውን የተዋሰስ ከሆነስ፧ የቅጅ ቅጅ ሊሆን አይችልም ወይ፧
፫ኛ/ ለመሆን ለስንት መቶ አመታት ያህል በግእዝ (በግዕዝ) ሆሄያት ተጠቅመናል፧ (?) ለአማርኛ ቋንቋ። ፊደላቱ የአማርኛን ቋንቋን እንደራሱ ማለት እንደ ቋንቋው ባህርይ አጢኖ ገበተናወም ለዚሁ ጉዳይ ታስቦና እንዲጠቅም ተደርጎ የተሰራበት ዶሴ አለ ወይ፧

ከላይ የተጠቀሱት ጥያቄቶች ከሞላ ጎደሉ ነው። ጥያቄዎቹም ለእናንተ ጥያቄ የመነሳት ምክንያት የሚሰተዋሉበትን ጥያቄዎች ናቸው።+

ችግሩ ከዋናው ከመሰረቱ ነው። ስለሆነም፣ ስህተታችሁ በሀገር የመጣ ሲሆን፣ በቀላሉ ተሳስታችኋል ሊባል ይቻልም። እንዲያውም ችግሩንም እንደመጠቆም ወደ መህትሄውንም እንደመስጠት ሞክራችኋል ትክክል ባይሆንም¡ ወደ ቀናው መንገድ ግን ይመራናል። እኔም ለመጻፍ በቃሁ። ሌላውም የራሱን ይላል። ወደ ምንስማማበት ሰፈር እንደርሳለን።

የንግግርና የጽሁፍ አግባባቸው የተለያዩ የሚሆንበት አጋጣሚ አለ። ይህ አጋጣሚ ግን፣ ያልተስተዋለ ለውጥ ማምጣት የለበትም(ሀ፣ሃ ወይም አ፣ኣ)። ድምፅ የመመሳሰል ባህሪይ ሲኖረው ሆሄያት ግን የላቸውም፣ ምክንያቱን ድምጹን እንዲወክል ተብሎ ከጅምሩ ስለተቀረጸ ለይቶ ሊያስቀምጣቸው የግድ ይላል። ካልሆነ ግን አልተሟላም ለማለት ይቻላል። በተለይ የአማርኛ ቋንቋ እና የግእዝ ሆሄያት ትብብር የድምፅን መመሳሰልን፣ በፅሁፍ ወቅት ልዩነቱን በግልጽ የማሳየት አቅማቸው የላቀ ነው። እንዴት፧

አ ለሚለው ግዕዝ፣ ሰባት ተጨማሪ የድምዕ አከሎበት፣ የአን ጓድ ብቻ ሰምንት የተለያያ ድምፅ ወካይ (ሆሄ) በመስጠት። አ የሚባለው ግእዝ ይጠናቀቃል። አ ኡ ኢ ኣ ኤ እ ኦ ኧ።

አ ኡ ኢ ኣ ኤ እ ኦ ኧ
በ ቡ ቢ ባ ቤ ብ ቦ ቧ
ሀ ሁ ሂ ሃ ሄ ህ ሆ ሇ
ረ ሩ ሪ ራ ሬ ር ሮ ሯ

አሁን ሰህተቱን በምሳሌ ለማስረዳት እሞክራሁ።

አበበ፡ አበበ የሚለው ንባብ እንመልከት።

አ፥ በዚህ ንባብ ውስጥ እራሱ አን የሚለውን ሆሄ ወክሎ ነው የሚሰራው። አ የሚለው ግዕዝ-ሆሄ፣ የቃሉን ትርጉም ይለውጣል። መጣ፣ ለሚለውው ንባብ፣ አ ከተጨመረበረት ትርጉምን ይቀይራል ማለት ነው። አመጣ

በ፥ በዚህ ንባብ ውስጥ እራሱን በመድገም ነው የገባው። ይህ ደግሞ ለቃሉ አንዳይነት ባህርይ ያጎናጽፈዋል። አዝግሞ የሚለወጥ ነገርን ይጠቁማል። የቃሉን ትርጉም ባናውቀውም እንኳን፣ ባህርዩን እንድናስረውል ያደርገናል።

በ፥ በዚህ ንባብ ውስጥ እራሱን የደገመው በ፣ ለቃሉ የሚሰጠው ባህርይ በምሳሌ እንመልከት። ደበበ፣ መዘዘ፣ ለዘዘ፣ በረረ…። ልብ ይበሉ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚደገመው የመጨረሻው አንድ ሆሄ ብቻ ነው። ሁለቱም የሚደጋገሙበት ግዜ አለ። ፈተፈተ፣ ከተከተ፣ ለመለመ፣ ወዘወዘ…

አበባ፥ የሚለውን ስንመለከት ደግሞ በ፣ እረሱን ደግሞና አን፣ አስከትሎ ነው ወይስ የራሱን ራብዕ-በን፣ ተጠቅሞ ነው። አበበአ ወይስ አበባ። ብዙ የትርጉም ልዩነት ሳያመጣ የቃሉን ባህሪይ ቀየር ያደርገዋል። ባ፥ የቃሉን ባህሪይ ሲገልጸው፣(አ ከፊታቸው ያሰለፉና ወይም ማንኛው በራብዕ ረድፍ ላይ ያለ ሆሄ) የድርጊትን መደረግንና ድርጊቱም የመቀጠል ባህርይ እንዳለው ይናገራል። ለነገሩ ባለ አንድ ፊደል ባለ ሁለት ፊደል ባለሶስት ፊደል ቃላት የየራሳቸው የሆነውን ባህርይ ይገልጻሉ። ይህ ደግሞ አማርኛን ያልቀዋል። ገባ፣ ወጣ፣ ገዛ፣ ለዛ፣ ገበጣ፣ ሾጣጣ፣ ለማጣ… ድርጊቱ ያለና የሚቀጥል መሆኑን ያሳያል።

ሰለዚህ እንደ ኣ እና ሃ ያሉት ሆሄያት በተገቢ ቦታቻው ላይ ከተቀመጡ፣ ማለት በራብዕ ጎራ ላይ የባህርዩን ይጎናጸፋሉ ማለት ነው። ና በረሀ ብለን ብንጽፍ ወይስ በረሃ ብለን ብንጽፍ የተሻለ ነው፧ ራብዑ ሀ ወይም ሃ፣ የመሞቅና ጉዳዩም የመቀጠሉን ነገር ስለሚያስረተውል የተሻለ ሳይሆን አይቀርም። ተሳስታችዃልን የተሻለ ሳይሆን አይቀርም ብዬ መልሱን የደመከምኩላችሁ፣ ስህተቱ ያለው ከላይ ከ ፩ እስከ ፫ የተጠቀሱት ላይ በመሆኑ ነው።

ጥሩ ትችት ይመስላል። ስለ ፣ እና ፊደል አመጣጥ ፈቃደ ጥሩ ጽሑፍ አቅርቧል። ፊደሎቹ ላይ ይጫኑ። ኸ እና ኧ በግዕዝ እሚገኙ ፊደላት አይመስሉኝም። የሐ እና ሀ አጠቃቀም በየዘመናቱ ተቀይረዋል። በጥንቱ አማርኛ የነበራቸው አጠቃቀምና አሁን ያላቸው ይለያያል። በኔ በኩል የደራሲ ሀዲስ አለማየሁን አስተያየት እቀበላለሁ። እርሱም ተደጋጋሚ የሆኑ ፊደላትን መተውና ወጥ በሆነ ሁኔታ መቀጠል የሚለውን ነው። ሆኖም አንተ ባልከውም እስማማለሁ። ማለትም አንድ መደበኛ ወጥ ሰዋሰውና አንድ መደበኛ ወጥ ስነ ፊደላት ቢኖር ጥሩ ነው። ችግሩ የትም ቋንቋ ቢኬድ፣ ሥነ ፊደላት፣ ኢ-አምክንዮዋዊ መሆኑ ነው። Hgetnet 00:39, 9 ፌብሩዌሪ 2012 (UTC)[reply]

ጥሩ ውይይት ነው፣ ስሕተትም መታረም ኣለበት። ስለ "ሀ" እና "አ" በዶ/ር ኣበራ ሞላ የተጻፈም እዚህ ኣለ።