ውይይት:የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ
Hgetnet፣ Elfalem፣ ፈቃደ ይህ ጽሑፍ ሙሉ በሙሉ የፖለቲካ አቅዋምን ለማራመድ የተዘጋጀ ጽሑፍ እንጂ በዊኪፔድያ መርህ መሠረት በገለልተኝነት መንፈስና ሚዛናዊ በሆነ አጻጻፍ አልተዘጋጀም። ጽሑፉ በዊኪፔዲያ መርህ ተቀባይነት እንዲኖረው በጥንቃቄ መታረምና መመልመል ይገባዋል። ችላ ተብሎ የታለፈ እንደሆነ ዊኪፔዲያ የፖለቲካ መድረክ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ማኒፌስቶ ማራመጃ ስለሚሆን አስቸክዋይ እርምጃ እንዲወሰድ አሳስባለሁ።--Bulgew1 (talk) 01:14, 3 ፌብሩዌሪ 2013 (UTC)
- ገጹ ወደኋላ ዕትም ተመልሷል። Elfalem (talk) 08:30, 3 ፌብሩዌሪ 2013 (UTC)
፡Hgetnet፣ Elfalem፣ ፈቃደ ይህ ጽሑፍ አሁንም ተመልሶ እንደገና የፖለቲካ አቅዋምን ለማራመድ የተዘጋጁ ዕርማትን አካቷል። አሁንም የዊኪፔድያን መርህ በመከተል በገለልተኝነት መንፈስና ሚዛናዊ በሆነ አጻጻፍ አልተዘጋጀም። ዊኪፔዲያን የፖለቲካ መድረክ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ማኒፌስቶ ማራመጃ ማድረግ ተፈልጎ ከሆነ መርሑ ግልጽ ይደረግና ፖለቲካዊ መረጃችንን ከዊኪፔዲያ ማግኘት የማንጠብቅና የማንፈልግ አባላት ተሳትፏችንን እንተወው። የኔ ተቃውሞ ትክክል ከሆነ ግን ይሄንን ዓይነት የፖለቲካ ማኒፌስቶ ወይም ፖለቲካዊ ድርጅታቸውን በዊኪፔዲያ አማካይነት ለማስተዋወቅ የሚጥሩትን በማያደጋግም እርምጃ አሳውቁልን/አስቁሙልን። አመሰግናለሁ--Bulgew1 (talk) 14:01, 24 ማርች 2013 (UTC)
- ሰላም Hgetnet፣ Elfalem፣ ፈቃደ ፦ Demhitvic ትናንት «የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ] የሚያሳውቀው የኢሃኣዴግ ስርዓት ከስልጣን የሚለቀው በጥትቅ ትግል እንጂ በፖለቲካ ተደራድሮ እንዳልሆነ፣ ለመላው [[1]] ህዝብ ሆነ የፖለቲካ ድርጅቶችን ያሳውቃል፣ ስለዚ የያዘው የትጥቅ ትግል ስርዓቱ እስከሚገረሰስ እበርትቶ እንደሚቀጥል ያሳውቃል፣» በሚል ያሠፈረ/ች/ውን ለውጥ 'ዓይን-አውጣ' ማስታወቂያ በመሆኑ ሰርዠዋለሁ። Demhitvic እንደዚህ ዓይነቱን መልክት ማስተላለፍ ያለባ/በ/ት በአማርኛው ዊኪፔዲያ ላይ እንዳልሆነ ያስረዳል ብዬ እገምታለሁ። --Bulgew1 (talk) 09:48, 25 ማርች 2013 (UTC)
- Bulgew1፣ ያቀረባቸው ነጥቦች ትክክል ናቸው። ውክፔዲያ በተፈጥሮው ማንው ሰው የሚያርመው ስለሆነ እንደዚህ ዓይነት መርህን የሚጥሱ ዝግጅቶች በየጊዜው ይታያሉ። በአሁኑ ሰዓት ይህ ገፅ ከመጋቢዎች ውጭ ከመታረም ተቆልፎአል። Elfalem (talk) 08:02, 26 ማርች 2013 (UTC)