ውይይት:የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
በታም መልካም ነገር ነው የተመለከትኩት እና በዚህ ቀትሉበት እላለሁ ነገር ግን በኢትዮዽያ አርቶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 81 የመጽሐፍ ቅዱስ ቁጥር እንደምትቀበል ተገልጿል ድምሩ ላይ ትክክል ነው:: የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ቁጥር ግን 35 ተብሎ ቢስተካከል መልካም ይመስለኛል::
፣፣ '''
"በቅርብ ጊዜ"
[ኮድ አርም]አባል:Codex Sinaiticus፣ አባል:Elfalem፣ አባል:Hgetnet
መስከረም ፪ ቀን [አባል:Ethiopia1234] የጨመረ/ች ው ኃተታ አንድ ጎን ብቻ የሚያሳይ፤ ክርክርን የሚስብ እና ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት፣ ታሪክ፣ አመሠራረት፣ አስተዳደር፣ ሂደት፣ ወ.ዘ.ተ. በገጹ ላይ የምናገኛቸውን አወንታዊ ትንተናዎች የማያስፋፋ ኃተታ ነው። ጽሑፉ ምናልባት «አለቃ አያሌው ታምሩ» ገጽ ላይ ቢጨመር የተሻለ ይሆናል እንጂ በዚህ በ«የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን» ገጽ ላይ "የአስተዳድር ተቃውሞ" ወይም "የአምስተኛው ፓትርያርክ ተቃዋሚዎች" ወይም ሌላ ተመሳሳይ ንዑስ ርእስ ስር ባጭሩ፤ በአወንታዊ ዘገባ ስልት፣ «አለቃ አያሌው ታምሩ ሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፻፹፰ ዓመተ ምሕረት በ«መብሩክ» ጋዜጣ ላይ መላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ከፓትርያርኩና ተከታዮቻቸው ቃልና እጅ ቡራኬ እንዳይቀበል በአብ፥ በወልድ፥ በመንፈስ ቅዱስ ሥልጣን፥ በጴጥሮስ፥ በጳውሎስ፥ በማርቆስ፥ በቄርሎስ፥ በባስልዮስ፥ በቴዎፍሎስ፥ በተክለ ሃይማኖት ዘደብረ ሊባኖስ ቃልና በራሳቸው ማውገዛቸውን አስታወቁ።» የሚል አረፍተ ነገር ብቻ የሚበቃ ይመስለኛል። ስለዚህ ብንወያይበትና በጉዳዩ ውሳኔ ብትሰጡበት ጥሩ ነው። --Bulgew1 12:48, 15 ሰፕቴምበር 2011 (UTC)
- ይህ ኃተታ ከሌላ ምንጭ በቀጥታ የማብዛት ፈቃዱ ሳይታወቅ የተገለበጠ ስለሆነ በውክፔዲያ ላይ መኖር የለበትም። Bulgew1 እንደሚለው አንድ የሚያጠቃልል አረፍተ ነገር ቢቀመጥ ይሻላል። Elfalem 03:45, 16 ሰፕቴምበር 2011 (UTC)
- ስምምነት ስላለ አጥፍቸዋለሁ
- ይህ ኃተታ ከሌላ ምንጭ በቀጥታ የማብዛት ፈቃዱ ሳይታወቅ የተገለበጠ ስለሆነ በውክፔዲያ ላይ መኖር የለበትም። Bulgew1 እንደሚለው አንድ የሚያጠቃልል አረፍተ ነገር ቢቀመጥ ይሻላል። Elfalem 03:45, 16 ሰፕቴምበር 2011 (UTC)
። Hgetnet 00:27, 17 ሰፕቴምበር 2011 (UTC