ዙሪክ

ከውክፔዲያ
የዙሪክ ከተማ አርማ

ዙሪክ (Zürich) በስዊስ አገር የሚገኝ ከተማ ነው። በስዊትዘላንድ ከሁሉ ታላቁ ከተማ ነው። የከተማው ሕዝቡ ቁጥር 380,500 ሰዎች ሲሆን፣ በአካባቢው በጠቅላላ 2 ሚሊዮን ያሕል አሉ።

ከተማው በሮሜ ሰዎች በ7 ዓ.ም. ሲመሠረት ስሙን ቱሪኩም አሉት። በ1520ዎቹ፣ የፕሮቴስታንት እንቅስቃሴ ማዕከል ሆነ። የፕሮቴስታንት ሰባኪ ኡልሪክ ዝቪንግሊ ከዙሪክ ነበረ።

ዙሪክ ከአለሙ ሁሉ አንደኛው ሀብታም ከተማ መሆኑ ይቆጠራል። የኗሪዎች ዋና መነጋገሪያ አለማንኛ ነው።