ዛምቢያ (የኢሲን ንጉሥ)
Appearance
(ከዛቢያ የተዛወረ)
ዛምቢያ ከ1749 እስከ 1747 ዓክልበ. ድረስ የኢሲን ንጉሥ ነበረ። በሱመር ነገሥታት ዝርዝር መሠረት ለ3 አመት ብቻ ነገሠ። ከተገኙትም የአመት ስሞች የተነሣ ከ2 ወይም 3 አመት በላይ እንዳልነገሠ ይመስላል። ዛምቢያ ኤንሊል-ባኒን ተከተለው። በመጨረሻው አመት (1747 ዓክልበ.)፣ የተፎካካሪውን ከተማ ላርሳን ሃይል ለመቃወም ዛምቢያ ከባቢሎን፣ ኤላምና ካዛሉ ጋር ተባበረ፤ የላርሳ ንጉሥ ሲን-ኢቂሻም ግን ድል አደረጋቸው። ከዚያ በኋላ ኢተር-ፒሻ ዛምቢያን በኢሲን ተከተለው።
ቀዳሚው ኤንሊል-ባኒ |
የኢሲን ንጉሥ 1749-1747 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ ኢተርፒሻ |