ዝግመተ ለውጥ

ከውክፔዲያ
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎችፍለጋ
፫ቱን የሕይወት ዓይነቶች እሚያሳይ ምስል

የአንድ ሕይዎት ያለው ማህብረሰብ የዘር ውርስ ባህሪይ ከትውልድ ወደትውልድ እየተቀየረ መሄዱ ዝግመተ ለውጥ ይባላል። ቻርለስ ዳርዊን ይህን ኩነት በማስተዋልና በሳይንሳዊ አመክንዮ አሰደግፎ በመተንተኑ የመጀመሪያው ሰው ነው። ዳርዊን በተጨማሪ የተፈጥሮ ምርጫ ባለው ኅልዮቱ ሕይዎት ያላቸው ማህበረሰቦች ዝግመተ ለውጥ እሚያካሂዱት ምንም እንኳ በዘፈቀደ ስህተት እየፈጸሙ ቢሆንም፣ ተፈጥሮ እራሷ በምትፈጥረው መሰናክሎች እኒህን መሰናክሎች አልፈው የሚሄዱትን በመምረጧ ነው። ዳርዊን የተፈጥሮ ምርጫን አስተሳሰብ ከ፫ የሚታዩ ነገሮች አንጥሮ ነበር ያወጣው፦ ፩) እንስሳትም ሆነ እጽዋት ወደፊት ሊኖር ከሚችሉ ዘሮች በላይ አተረፍርፈው ነው እሚራቡት ፪)ሕይወት ያላቸው እያንዳንዳቸው ነገሮች ሁልጊዜ የተለያየ ጸባይ ነው ያላቸው፣ ስለሆነም እያንዳንዳንቸው በቀጣይ የመኖር ዕድላቸው የተለያየ ነው ፫) ስለሆነም የአንድ ማህበረሰብ አባላት ሲሞቱ፣ የሚገላቸውን ነገር ጠንክረው እሚቋቋሙት ግለሰቦች ብቻ በሕይዎት ቆይተው ወደፊት መራባች ይችላሉ። ስለሆነም ቀስ በቀስ እነዚህ በህይዎት ያሉ፣ በህይዎት የሌሉትን አይነቶች እየተኩ ይሄዳሉ።

በ፳ኛው ክፍለ ዘመን ጄኔቲክስ እና ዝግመተ ለውጥ ተዋህደው ማህበረሰባዊ ጄኔትክስ እሚባለውን ጥናት ለመፍጠር ችለዋል። አንድ ማህበርሰብ ለየት ያለ ግለሰቦችን ለመፍጠር ከሚያስችሉት መንገዶች አንዱ ሙቴሽን የተባለው ሂደት ሲሆን፣ ሙቴሽን እሚፈጠረው የዚያ ግለሰብ ዲ ኤን ኤ ከወላጆች ሲዎረስ በሚደረግ ስህተት ነው።