የመረጃ ኅብረተሠብ

ከውክፔዲያ

የመረጃ ኅብረተሠብ ማለት ዘመናዊ የመረጃና የመገናኛ ቴክኖዎሎጂ አይነተኛ ሚና የሚጫወትበት ኅብረተሠብ ነው። በዚሁ ኅብረተሠብ ውስጥ በምጣኔ ሀብት ረገድ የተነገደው ሸቀጣሸቀጥ ወይም የሚዛወረው ዋና ጥቅም ተጨባጭ ዕቃ ሳይሆን የመረጃዕውቀት ማሠራጨት እራሱ ይሆናል።

ብዙ ጊዜ የአሁኑ ዓለም «የመረጃ ኅብረተሠብ» ከ18ኛው ክፍለ ዘመን ጀመሮ የተካሔደው የኢንዱስትሪ አብዮት ተከታይ እንደ ሆነ ይቆጠራል።