የመዋጋት ወይም መሸሽ መልስ
Appearance
የመዋጋት ወይም መሸሽ መልስ አሜሪካዊው መምህር ዶ/ር ዋልተር ካኖን በ1908 ዓም የገለጠ ሃልዮ ነው። በመላምቱ ዘንድ እንስሶች አደጋ ባጋጠሙበት ጊዜ በቅጽባት እንዲዘጋጁ ለመርዳት የእድገንጥር ጐርፍ ከአዕምሮና ከኩላትጌ ዕጢ (አድሬናል ግላንድ) ያገኛሉ።
ይህ ሁሉ እንስሳ በአደጋ ሰዓት እንዲዘጋጅ ስለሚረዳ፣ ለእንስሳው ጥቅም እንደተለማ ይታስባል። ይህም በእድገ-ንጥር (ሆርሞን) እንደ ተሠለጠነ ይባላል።
ነገር ግን ለሰው ልጆች በተያዘ፣ የተዘረዘሩት ውጤቶች ሁሉ ምንም ጠቃሚ አይደሉም። ባጭሩ የሽብር ፍዳ ምልክቶች ናቸው፦
- የልብ ምት ማፋጠን፣
- የፊኛ መፈታት፣
- ዋግምቦ እይታ - የዘርፋዊ እይታ ፈዘዛ፣
- መንቀጥቀጥ፣
- የብሌን መስፋት፣
- የቀላ ፊት፣
- ደረቅ አፍ፣
- የሆድ መፍጨት ቆይታ፣
- የጆሮ መስማት ቅንሰት
እነዚህም ውጤቶች ደግሞ በእድገ-ንጥሮች እንደ ተሠለጠኑ ይባላል። ስለዚህ በተቃራኒ ለሰው ልጆች ጠቃሚ የሆኑት ውጤቶች ቢሠለጠኑ ኖሮ እንዲህ ይሆናሉ፦
- ልቡ ሳይሸበር በጸጥታ መወሰን፣
- የፊኛ መጠበቅ፣
- ዓይኑን አለማጭበርበርና በቶሎ ትክተቱን ማግኘት፣
- የጆሮ ፈጣን ማዳመጥና ማስተዋል፣
- ወደ ኋለ የሚቀር ጎጂ ደመነፍስን መቆጣጠር።